18.8.15

የልጅነት ትዝታ… ሙልሙል ዳቦ


"ሆያ ሆዬ  ሆ  ሆያ ሆዬ ሆ
እዛማዶ ጭስ ይጨሳል
አጋፋሪ ይደግሳል
ያንን ድግስ ውጬ ውጬ
በድንክ አልጋ ተገልብጬ
ያችም ድንክ አልጋ አመለኛ
ያለ አንድ ሰው አታስተኛ"


አልኩና ሙልሙሌን እንደ ልጅነት ትዝታዬ በሻይ እያጠቀስኩ በላሁ።


የልጅነት ትዝታ ለካስ ይበላል… ይገመጣል…  የኮባው ቅጠል፥ የጭሱ ቃና ሁሉ ሲጣፍጥ 


እንኳን አደረሳችሁ።

በረከት