20.4.15

ከእግዚአብሔር ነንና እናሸንፋቸዋለንክርስቶስን በማምለክ እንጸና ዘንድ፥ ማድረግ የሚገባንን እናደርግ ዘንድ፥ ማስብ ያለብንን እናስብ ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ልቦና ይሰጠን።
በጸሎትን ጸንተን አቤቱ የማያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው የሚል በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ልቦና ይሰጠን። ጸሎታችንን ልመናችንን ሀዘናችንን በጌታችን መንበር ፊት ትድረስ። 

ወገኔ ተነስ እጅህን አንሳ... ከእኛ ጋር ያለው ታላቅ ነው 
ከእኛ ጋር ያለው የሚረዳንና የሚዋጋልን ነው።

 ከእግዚአብሔር ነንና እናሸንፋቸዋለን፥ ከእነርሱ ካለው ይልቅ በእኛ ያለው ታላቅ ነው። ወገኔ ሆይ ተነስ... እጃችንን እናንሳ!
ከእግዚአብሔር  ጋር  ህብረት በማድረግ  ድል ይገኛልና ይህንን ለማየት....  ለመመልከት ከፈለግን ለጸሎት እጃችን 
ጸሎት እናንሳ!  
 በእኛ ውስጥ እና ከእኛ ጋር የሚሠራ እርሱ ነውና
ለጸሎት በጸሎት  እጃችንን እናንሳ! 
 ከእግዚአብሔር ነንና እናሸንፋቸዋለን። 

በረከት 
No comments:

Post a Comment