20.4.15

ከእግዚአብሔር ነንና እናሸንፋቸዋለንክርስቶስን በማምለክ እንጸና ዘንድ፥ ማድረግ የሚገባንን እናደርግ ዘንድ፥ ማስብ ያለብንን እናስብ ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ልቦና ይሰጠን።
በጸሎትን ጸንተን አቤቱ የማያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው የሚል በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ልቦና ይሰጠን። ጸሎታችንን ልመናችንን ሀዘናችንን በጌታችን መንበር ፊት ትድረስ። 

ወገኔ ተነስ እጅህን አንሳ... ከእኛ ጋር ያለው ታላቅ ነው 
ከእኛ ጋር ያለው የሚረዳንና የሚዋጋልን ነው።

 ከእግዚአብሔር ነንና እናሸንፋቸዋለን፥ ከእነርሱ ካለው ይልቅ በእኛ ያለው ታላቅ ነው። ወገኔ ሆይ ተነስ... እጃችንን እናንሳ!
ከእግዚአብሔር  ጋር  ህብረት በማድረግ  ድል ይገኛልና ይህንን ለማየት....  ለመመልከት ከፈለግን ለጸሎት እጃችን 
ጸሎት እናንሳ!  
 በእኛ ውስጥ እና ከእኛ ጋር የሚሠራ እርሱ ነውና
ለጸሎት በጸሎት  እጃችንን እናንሳ! 
 ከእግዚአብሔር ነንና እናሸንፋቸዋለን። 

በረከት 
11.4.15

2015, Ethiopian Easter

የአብርሃም አምላክ የይሥሐቅም ቤዛ
ወገኖቹን ሁሉ በራሱ ደም ገዛ

ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ።

በረከት


3.4.15

Easter egg


ከእለታት አንድ ቀን... አምስት እንቁላሎች ተጣሉ (ተወለዱ)። 


እናቲቱም ተቀምጣባቸው ታሞቃቸው ጀመር።


ከአንድ... ሃያ ቀናቶች በሓላ እንቁላሎቹ መፈልፈል ጀመሩ።አንደኛው ከሁሉም ቀድሞ ተፈልፍሎ ሌሎቹን ከእናቱ ጋር መጠበቅ ጀመረ።


አንድ በአንድ ተፈለፈሉ።


አራቱ ተፈልፍለው.... 


ያልተፈለፈለውን አንዱን እንቁላል መጠበቅ ጀመሩ።


እናትም በፍቅርና በትእግስት ብዙ ጠበቀች፥... 


 ወገኖቹም አብረው ጠበቁ።  ሰዕቱ አለፈ፥ ብርሀን እየራቀው መጣ ። 


እሷም የተፈለፈሉትን ጫጩቶቿ ይዛ ሄደች።


ያልተፈለፈለው  እንቁላል ብቻውን ቀረ። ብርሀን በራቀው ቁጥር ጨለማ ከበበው። 

"For God so loved the world that he gave his one and only Son, that whoever believes in him shall not perish but have eternal life."

John 3 16

"በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔርአንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና"
የዮሐንስ ወንጌል 3:16