2.3.15

የጀግና ሽልማቱ"መልካም ስም ከመልካም ሽቶ ይበልጣል" እንደተባለው ይህንን መልካም ስማችንን ያቆዩልን፥ ዛሬ እየፎከርን የምናቅራራበትን "ኢትዮጲያዊውን" ስም  አውርስውንና ከትበውን የሄዱት ጀግኖች ምን ተከፈላችው?

የጀግና ሽልማቱ ነፃነቱ፥ የጀግና ሽልማቱ ሀይማኖቱ፥ የጀግና ሽልማቱ ተስፋው.... መሆኑን ስለገባችው... ያለአንዳች ሽልማት ይህንን እፁብ ታሪክ ስሩ። አዎን አንዳንዶች ለዝናና ለክብር አድርገውታል ያም ቢሆን በሰዐቱ ሽልማታቸው ነበር።
ወገኔ ሆይ! እነዚያ ጀግኖች ያፈስሱት ቆራጥና ውብ ደማቸው ለከንቱ አታድርገው። ዛሬም ቢሆን ሽልማትህ....  ነፃነትህ፥ ሀይማኖትህና ተስፋህ ነው። ለገንዘብ ለከንቱ ውዳሴና ዝና ብለህ አገርህን አታራቁት። ጎሳ ዘር እያልክ አገርህን የምትቀረጣጥፍ ሁሉ ዋጋህን ሳትቀበል በፊት ንቃ።
 አንዲቷ ሀገርህ ጎሳህ ናት  አንዲቷ ሀገርህ ዘርህ፥ እናት ወገንህ ናትና አታቦጫጭቃት ሓላ ትጠየቅበታለህ።  ጀግናዎቹ ያፈስሱት ቆራጥና ውብ ደማቸው ለከንቱ አታድርገው። "መልካም ስም ከመልካም ሽቶ ይበልጣል" እንደተባለው ያንን መልካም ስማችንን ዛሬም መልካም አድርገህ ለነገው ትውልድ አቆይ።
MAGE CREDITS: GOOGLE.COM, PHOTO TINTING BY BEREKET MAMO
ቸሩ ፈጣሪ አምላካችን ሀገራችን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን።
ያባቶቻችን ቃል ኪዳን አይለየን። 

በረከት  


No comments:

Post a Comment