24.2.15

ያልፋል
ድሮ ብዙዎቻችን ባቡሩን ከማየታችን በፊት “እልም አለ ባቡሩ” የሚባለውን ግጥም ስምተናል። አሁን አድገን…. እንኳን ባቡር…. ግዜም እልም ሲል አይተናል። ህይወትም…. እንደዋዛ ሽው ብላ ስትሄድ ስሚዎች ብቻ ሳንሆን ተመልካⶇች የሆንን ስንት እንሆን ይሆን?
የማያልፍ የለም ሁሉም አለፊ ነው። አንዳንዴ እስኪያልፍ ያለፋል እያልን ወይም እየተባልን ማሳለፋችን የማይቀር ነው።  
አዎን እስኪያልፍ ያለፋል.... እንዴት ነው የማያለፋው? ግን ያልፋል!  በዘመናችን እንኳን ስንቱ ነገር ነው ያለፈው? እንደባቡሩ ሁሉም ያልፋል። ሀዲዱ ይቆይ ይሆናል ጠባሳውና ስብራቱ ይታይ ይሆናል፥ ግን ያልፋል።


ለቅሶ በዝማሬ በእልልታ ታጅቦ
ሃዘን መቆዘምም በደስታ ተውቦ
ግዜውን ጠብቆ መከራውም ያልፋል
አንተ ብቻ ታገስ ሁሉም ይቀየራል

ጠንከር ቆፍጠን ብለህ ወደ እልፍኝህ ግባ
በርህን ዝጋ እንጂ ለማንም አትባባ
አምላክ እረኛህ ነው ጠባቂ ከላይ
ሰላም ይስጥሃል ከአእምሮ በላይ 
ምህረትን የሚወድ የሰራዊት  ጌታ
አለህ ካጠገብህ አንተ ብቻ በርታ

ወገኔ ሆይ! አይዞህ!
እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል። በውካታ በጫጫታ ውስጥ ስላምህ በዝቶ ታንቀላፋለህ።
በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል ተብሏልና  አንተ ብቻ በርታ። አንተ ብቻ በአምላክ ጥላ ውስጥ እደር። ሁሉም ያልፋል ወገኔ ሆይ! አይዞህ!

ይህንን ስእል ፎቶ አነሳሁት እንጂ እኔ አልሳልኩትም 

በረከት

No comments:

Post a Comment