24.2.15

ያልፋል
ድሮ ብዙዎቻችን ባቡሩን ከማየታችን በፊት “እልም አለ ባቡሩ” የሚባለውን ግጥም ስምተናል። አሁን አድገን…. እንኳን ባቡር…. ግዜም እልም ሲል አይተናል። ህይወትም…. እንደዋዛ ሽው ብላ ስትሄድ ስሚዎች ብቻ ሳንሆን ተመልካⶇች የሆንን ስንት እንሆን ይሆን?
የማያልፍ የለም ሁሉም አለፊ ነው። አንዳንዴ እስኪያልፍ ያለፋል እያልን ወይም እየተባልን ማሳለፋችን የማይቀር ነው።  
አዎን እስኪያልፍ ያለፋል.... እንዴት ነው የማያለፋው? ግን ያልፋል!  በዘመናችን እንኳን ስንቱ ነገር ነው ያለፈው? እንደባቡሩ ሁሉም ያልፋል። ሀዲዱ ይቆይ ይሆናል ጠባሳውና ስብራቱ ይታይ ይሆናል፥ ግን ያልፋል።


ለቅሶ በዝማሬ በእልልታ ታጅቦ
ሃዘን መቆዘምም በደስታ ተውቦ
ግዜውን ጠብቆ መከራውም ያልፋል
አንተ ብቻ ታገስ ሁሉም ይቀየራል

ጠንከር ቆፍጠን ብለህ ወደ እልፍኝህ ግባ
በርህን ዝጋ እንጂ ለማንም አትባባ
አምላክ እረኛህ ነው ጠባቂ ከላይ
ሰላም ይስጥሃል ከአእምሮ በላይ 
ምህረትን የሚወድ የሰራዊት  ጌታ
አለህ ካጠገብህ አንተ ብቻ በርታ

ወገኔ ሆይ! አይዞህ!
እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል። በውካታ በጫጫታ ውስጥ ስላምህ በዝቶ ታንቀላፋለህ።
በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል ተብሏልና  አንተ ብቻ በርታ። አንተ ብቻ በአምላክ ጥላ ውስጥ እደር። ሁሉም ያልፋል ወገኔ ሆይ! አይዞህ!

ይህንን ስእል ፎቶ አነሳሁት እንጂ እኔ አልሳልኩትም 

በረከት

21.2.15

vegan bean burritos, የጾም


Warm flour tortillas, በስሱ የተጋገረ ቂጣ


spoon some brown rice down the middle, ሩዝ  


Top the rice with black beans... የተቀቀለ ጥቁር ባቄላ 

          (mash the beans with a potato masher or fork, adding 3 to 4 tablespoons of the reserved bean liquid to make a thick, lumpy mixture. Add the diced tomato, minced seeded jalapeño chile pepper, lemon juice, garlic clove minced , finely diced fresh cilantro and salt…. mix well.) 

Avocado, አቨካዶ 

Shredded cabbage, የተከታተፈ ጥቅል ጎመን


and add your favorite salsa...hemmmRoll like a burrito as tight as it will go and...enjoy, ከበላህና ከጠገብህ በኃላ … አምላክህን እግዚአብሔርን አስብ። 
ኦሪት ዘዳግም 8:11

When you have eaten and you are full… then you shall bless the Lord
Deuteronomy 8:11
15.2.15

Shero
መልካም ቅበላ
ጾማችን የመንፈሳዊ ፍሬ ያፈራ ዘንድ እንዘጋጅ።   


በረከት 9.2.15

የክብሪት ቁንጅና
ምንም ብትቆነጅ ውብትህ ቢበዛ
ሳትቃጠል አትቀር እንዲህ እንዋዛ።

አንዳችን ለአንዳችን መስላል፥ አንዳችን ለአንዳችን ብርሀን፥
 አንዳችን ለወገናችን ወገን ያድርገን። 
አሜን  

በረከት