18.9.14

ኩኩሉ... ነጋ መስከረም ጠባ


ሀሁ በልጅነት ቶሎ ጨረስኩና
ወንጌሉ ላይ ገባሁ ምንም ሳልረዳ
ቶሎ ቶሎ ብዬ አንብቤው ስጨርስ
ከቤቴ ወጣሁኝ እሰው ጋር ለመድረስ

ባህርን ተሻገርኩ በድቅድቅ ጭጋግ
ድንገት ሳላስበው ጋቢ ስፈልግ
ደፋ ቀና አልኩኝ ትጥቄን ወዲያ ጥዬ
ልብሱን ደራረብኩት ይሞቀኛል ብዬ

እንጀራም ተበላ ተጠጣ ውሀው
ወንጌሉ ተረሳ ጥበብ የሙላው
ዛሬ ነገ እያልኩ ቀኑን ስቆጥረው
ግዜ ቶሎ ሄደ ማንም ሳይጠራው

ከእለታት አንድ ቀን ቋሚ ስው ነኝና ኩኩሉ ን ስማሁት
በአርምሞ ቁጭ ብዬ ወንጌሌን ከፈትኩት

ቀዮ ቀለም ለቆ ጥቁር ብቻ ቀርቶ
ግዕዝ ተደምስሶ ቋንቋው ተለውጦ
አየሁት ወንጌሌን በአባራ ተውጦ። ኩኩሉ... ብሎ የሚጮኸውን የልቦና ደውል ይሰጠንና አይነ ልቦናችንን ይግለጥልን። ያኔ! አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤አቤቱ ይቅር በለኝ  ማለት እንጀምራለን።  አሁን ልጅነት የለም... ስለዚህም በአርምሞ የእግዚአብሔርን ቃል እናንብብ። ለስጋችን ትጥቃችንና ሙቀታችን፥ ለነፋሳችን የእለት እንጀራዋ ነውና ወንጌላችንን እንክፈት።  በረከት