25.9.14

መስቀልበልደቱ ፍስሐ  
በጥምቀቱ ንስሐ
በመስቀሉ አብርሃ

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም አደረስዎ
18.9.14

ኩኩሉ... ነጋ መስከረም ጠባ


ሀሁ በልጅነት ቶሎ ጨረስኩና
ወንጌሉ ላይ ገባሁ ምንም ሳልረዳ
ቶሎ ቶሎ ብዬ አንብቤው ስጨርስ
ከቤቴ ወጣሁኝ እሰው ጋር ለመድረስ

ባህርን ተሻገርኩ በድቅድቅ ጭጋግ
ድንገት ሳላስበው ጋቢ ስፈልግ
ደፋ ቀና አልኩኝ ትጥቄን ወዲያ ጥዬ
ልብሱን ደራረብኩት ይሞቀኛል ብዬ

እንጀራም ተበላ ተጠጣ ውሀው
ወንጌሉ ተረሳ ጥበብ የሙላው
ዛሬ ነገ እያልኩ ቀኑን ስቆጥረው
ግዜ ቶሎ ሄደ ማንም ሳይጠራው

ከእለታት አንድ ቀን ቋሚ ስው ነኝና ኩኩሉ ን ስማሁት
በአርምሞ ቁጭ ብዬ ወንጌሌን ከፈትኩት

ቀዮ ቀለም ለቆ ጥቁር ብቻ ቀርቶ
ግዕዝ ተደምስሶ ቋንቋው ተለውጦ
አየሁት ወንጌሌን በአባራ ተውጦ። ኩኩሉ... ብሎ የሚጮኸውን የልቦና ደውል ይሰጠንና አይነ ልቦናችንን ይግለጥልን። ያኔ! አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤አቤቱ ይቅር በለኝ  ማለት እንጀምራለን።  አሁን ልጅነት የለም... ስለዚህም በአርምሞ የእግዚአብሔርን ቃል እናንብብ። ለስጋችን ትጥቃችንና ሙቀታችን፥ ለነፋሳችን የእለት እንጀራዋ ነውና ወንጌላችንን እንክፈት።  በረከት

11.9.14

2007 Ethiopian Enkutatashe

በዚህ ዓመት... 2007...  ውስጣዊው ባሕርይዎትን፥  የልቦናዎን ሀሳብ፥  የአንደበቶን ቃል፥ 
የእጆችዎ ስራና የእግሮችዎ አረማመድ 
 ይባርክሎት። 
መልካም አዲስ አመት!

በረከት8.9.14

የሩፋኤል ዝናብ


"Raphael, one of the holy angels, who presides over the spirits of men."
The Book of Enoch 20:3
"በሰው ቁስል የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ሩፋኤል ነው" ሄኖ.6÷3

ሩፋኤል
ሩፋ ማለት ጤና፣ ፈውስ፣ መድኃኒት ማለት ሲሆን ኤል ሚለው በሌሎቹም መላእክት ስም ላይ የሚቀጠል ስመ አምላክ ነው።
መልአኬን በፊትህ እሰዳለሁ….. ስሜ በእርሱ ስለሆነ አታስመርሩት
ዘጸ.23÷20-22
ታዲያ ሩፋኤል የሚለው በጥምረት  ከአምላክ ለሰዎች የተሰጠ ፈውስ  የሚለውን ይተካል...እኛም ጳጉሜ 3 የምትዘንበዋ የሩፋኤል ጸበለ... ዝናብን ባላየንበት ወራቶች ውስጥ ዛሬ ደረስን። ስውነቴን ባይነካውም በአይነ ህሊናዬ ተጠመቅሁ። 
እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን።
የቅዱስ ሩፋኤል አማላጅነት አይለየን

በረከት

6.9.14

13th month, Ṗagume

ከሀገር እርቀን ያለነው ጳጉሜን ሳናጣጥማት፥ ጰ ጲ ጳ እንደህልም ታልፈብንና አዲስ ዓመትን እንቀበላለን።
 ሀገር ቤት... ሀገር እናት... ያለው ግን  
 አዲስ ዘመን ብቻ ሳይሆን አዲስ ተስፋን ለመቀበል፥ መስከረም ጠባ! ለማለት      
ሁሉም እንደአቅሙና እንደ ባህሉ ጉድ ጉዱ ይላል። ሀገር ቤት... ሀገር እናትም ሞቅ ሞቅ ትላለች። ትባረክልን...ትልቅ ዋጋ ተከፍሎባታልና ትባረክልን። ዋጋውን እንደከፈሉልን እንደአባቶቻችን እስቲ የእግዚአብሔርን ቃል እንጠብቅ፥ ቃሉንም በልቦናችን እናኑር። አዲስ ዘመን ብቻ ሳይሆን አዲስ ተስፋን ከባለቤቱ ለመቀበል ጉልበታችንን ኑሮአችንን... ሁለንተናችንን ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር እናዘጋጅ።

በረከት