19.8.14

ደብረ ታቦር


ክፈት በለው በሩን የጌታዬን
ክፈት በለው በሩን የጌታዬን
ክፈት በለው ተነሳ ያንን አንበሳ
ክፈት በለው ተነሳ ያንን አንበሳ

መጣና ባመቱ እንዴት ሰነበቱ ?
መጣና ባመቱ  እንዴት  ሰነበቱ ?
እዚህ ቤቶች ..
እንደምን ናችሁ ..
ባመት አንድ ቀን ..
መጣንላችሁ ..

ሆያሆዬ ቡሄ ጨዋታ ነው ልማዴ
ሆያሆዬ ቡሄ ጨዋታ ነው ልማዴ
ሆያሆዬ ቡሄ ሙልሙል ይላል ሆዴ
ሆያሆዬ ቡሄ ሙልሙል ይላል ሆዴ


ሆያሆዬ .. x4
ያመት ክብራችን ከጥንት የመጣ
የቡሄ ለታ ችቦ ሲወጣ
ከማምዬ ቤት ሙልሙሉ ይምጣ

ሆያሆዬ ቡሄ ጨዋታ ነው ልማዴ
ሆያሆዬ ቡሄ ሙልሙል ይላል ሆዴ
ሆያሆዬ ቡሄ ሙልሙል ይላል ሆዴ


ዓመት አውዳ ዓመት ድገምና ዓመት ድገምና
የአባብዬን ቤት ድገምና ዓመት ድገምና
ፍቅር ይሙላበት ድገምና ዓመት ድገምና
የማምዬን ቤት ድገምና ዓመት ድገምና
ስላም ይሙላበት ድገምና ዓመት ድገምና

ክበር በንስሀ ክበር በጽሎት
የነአባብዬን ቤት ጌታ ይግባበት
ክበር በንስሀ ክበር በጽሎት
የነየማምዬን ቤት ጌታ ይግባበትእንኳን አደረሳችሁ።

በረከት
No comments:

Post a Comment