29.8.14

ውሃና ብርሃን


ውሃና ብርሃንን አሳምሮ የስራ እግዚአብሔርን አመስግኑት 
 ምሕረቱ በእኛ ላይ ጸንታለችና፤ በየቀኑ... በየሰዓቱ... የእግዚአብሔርን ድንቅ ስራ አይናችን ታያለች ልባችንም ታስተውላለች። የእግዚአብሔርም እውነት ለዘላለም ትኖራለች  

በረከት

19.8.14

ደብረ ታቦር


ክፈት በለው በሩን የጌታዬን
ክፈት በለው በሩን የጌታዬን
ክፈት በለው ተነሳ ያንን አንበሳ
ክፈት በለው ተነሳ ያንን አንበሳ

መጣና ባመቱ እንዴት ሰነበቱ ?
መጣና ባመቱ  እንዴት  ሰነበቱ ?
እዚህ ቤቶች ..
እንደምን ናችሁ ..
ባመት አንድ ቀን ..
መጣንላችሁ ..

ሆያሆዬ ቡሄ ጨዋታ ነው ልማዴ
ሆያሆዬ ቡሄ ጨዋታ ነው ልማዴ
ሆያሆዬ ቡሄ ሙልሙል ይላል ሆዴ
ሆያሆዬ ቡሄ ሙልሙል ይላል ሆዴ


ሆያሆዬ .. x4
ያመት ክብራችን ከጥንት የመጣ
የቡሄ ለታ ችቦ ሲወጣ
ከማምዬ ቤት ሙልሙሉ ይምጣ

ሆያሆዬ ቡሄ ጨዋታ ነው ልማዴ
ሆያሆዬ ቡሄ ሙልሙል ይላል ሆዴ
ሆያሆዬ ቡሄ ሙልሙል ይላል ሆዴ


ዓመት አውዳ ዓመት ድገምና ዓመት ድገምና
የአባብዬን ቤት ድገምና ዓመት ድገምና
ፍቅር ይሙላበት ድገምና ዓመት ድገምና
የማምዬን ቤት ድገምና ዓመት ድገምና
ስላም ይሙላበት ድገምና ዓመት ድገምና

ክበር በንስሀ ክበር በጽሎት
የነአባብዬን ቤት ጌታ ይግባበት
ክበር በንስሀ ክበር በጽሎት
የነየማምዬን ቤት ጌታ ይግባበትእንኳን አደረሳችሁ።

በረከት
13.8.14

የወይን ጠጅ ቀለምINTERIOR DESIGN IMAGE CREDITSpinterest.com


ወይን ጠጅ ቀለም ( Purple ) የስማያዊና የቀይ ቀለም ድብልቅ ነው።ስማያዊ ቀለም ከህግ ጋር ሲያያዝ  ቀይ ቀለም ደግሞ ከፍርድና ከጦርነት ጋር ይያያዛል። ሰለዚህም በድሮ ግዜ በወይን ጠጅ ቀለም የሚስሩ ልብሶች የሚለብሱት 
የንጉሳዊ ቤተስቦችና የህግ ስዎች ብቻ ነበሩ።
በአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ... ወይን ጠጅ ቀለምን ቀይ ሲለው   
በእንግሊዘኛው መጽሐፍ ቅዱስ... ወይን ጠጅ ቀለም  Purple ይለዋል።   ለምሳሌ
ሰለ ልባም ሴት መጽሐፈ ምሳሌ 31፥ 22 ላይ   " ጥሩ በፍታና ቀይ ግምጃ ትለብሳለች" ሲል 
በእንግሊዘኛው "her clothing is silk and purple" ይለዋል
የማርቆስ ወንጌል 15:16  እና የዮሐንስ ወንጌል 19:2  ላይ 
" ቀይ ልብስም አለበሱት"  ሲል በእንግሊዘኛው " they put on him a purple robe " ይለዋል 
ወይን ጠጅ  ቀይ ግምጃ  ነው  ወይስ ቀይ ?

በረከት


8.8.14

ሰማያዊ ቀለም


 

NTERIOR DESIGN IMAGE CREDITS:pinterest.com


ፍቅሩን እያስብን እንተጋዘንድ  ስማያዊውን መስቀል ልባችን ላይ ይጥለፍልን   
ስማያዊውን የስማይ ቤት መንግስተ ስማያትን ያውርሰን።
አሜን 

በረከት 


2.8.14

አረንጓዴ ቀለም
አረንጓዴ ለብሶ ይጫወታል ዓሣ
ደብዳቤ ጻፉልኝ እንዳንረሳሳ....
INTERIOR DESIGN IMAGE CREDITS:pinterest.com


እንደ አረንጓዴ ቀለም የገባችሁበት ቤት ሁሉ ይለምልም።  
 የለመለመውን የፍቅር ካባ ያልብሳቹህ።

በረከት

1.8.14

ቢጫ ቀለም

INTERIOR DESIGN IMAGE CREDITS:pinterest.com

እንደ ቢጫ የሚያበራ... ብርሃንን የለበስው... ቅዱስ መላእክት በስተቀኛችሁ ይቁም...
 በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና ተብላልና

በረከት