11.7.14

የባህር ዛፍ ቅጠል


ለብዙ አመታት የቆየ ባህር ዛፍ... 


ቅጠሉ ቀስ በቀስ...


ቅርጽንና ቁመቱን  ይቀይራል...


ወቅቱን ጠብቆ...


ቅጠሉ ቀለሙን ቢለወጥም...


የራሱ ዛፍ ያላስዋበው ቅጠል...


ቅጠሉ ከረገፈ በሃላ...


በተለያየ ቀለም ይዋባል።ቀኞቻችሁ በደስታ ይሞሉ፥ በእግዚአብሔርና በስው ዘንድ የበራችሁ ሁኑ። 

በረከት

3.7.14

July 4th የነጻነት ቀን


"ይቺ አገር - የኛ አገር
አንዴ ´ምትቦካ - አንዴ ´ምትጋገር፤
ሲሻ ´ምትወድቅ - ሲሻ ´ምትሻገር
አንዴ ባንተ ነበር - አንዴም በኛ ነበር፤...


    

አገር እንደ ተረት - ‹‹ተረት›› ከተባለ
ተረት ነው አገርህ - በል ተርት ምናለ፤
አገር እንቆቅልሽ - ይሁን ከተባለ
‹‹እንቆቅልሽ አገር›› - ይኸውልህ አለ፤
አገር እንደ ፈሊጥ - ምሳሌ ከሆነ
ከኛዋ አገር በላይ - ምንም ‹‹ፈሊጥ›› የለ፤...


     

አንዱ ‹ሲተርታት› - እሳት ዳር ቁጭ ብሎ
አንዱ ይሰማዋል - ‹‹የመሰረት›› ብሎ፤
ሌላው ‹እንቆቅልሽ› - ሲያደርጋት ጨክኖ
‹ምን አውቅልህ?› ይላል - ያኛው ከጎን ሁኖ፤
ቀሪው እንደ ‹ፈሊጥ› - ቃል ሲያሳምርባት
ይኸ በምሳሌው - አለ ሲስቅባት።...ይቺ አገር - የኔ አገር
ይቺ አገር - የአንተ አገር
ይቺ አገር - የአንቺ አገር
ይቺ አገር - የኛ አገር / የሁላችን አገር /
አንዴ ስትቦካ - አንዴ ስትጋገር፤
በአቡኪና ጋጋሪ - ልኳ እየተለካ
ቀድሞ ባልተፈጨ - ሊጧ እየተቦካ
አለች እስከዛሬ - ሳትመር ሳትጥም
መጋገሪያው ምጣድ - ከሙግዱ ሳይገጥም። ...

     


ለዚያም ነው
የዚያኛውን አቡኪ - ይኸ እየጋገረው
ያ የጋገረውን - አንዱ እየሰበረው
በሰባራ ምጣድ - እንደ እንኩሮ እንጀራ
በመጣ፤ በሄደ - አገሬ ተጋግራ
ይህንን እንጀራ
የመጣ ጋጋሪ - ወይም ባለተራ
ለባለ አገር ሁላ - ቢያበላ፣ ቢያበላ
ጠኔ አላጠገገም - ራብም አልከላ!


    

    


ምክንያት፤
የአያቶቹን ምጣድ - አባት እየሰበረ
የአባቶቹን ምጣድ - ልጅ እየቀየረ
አገር እያቦካ - ቀዬ እየጋገረ
እልፍኝ እያበጀ - ከልካይ እያኖረ
አብሲቱን ህዝብ ግን - ይረሳው ነበረ፤...እና እንዲህ እላለሁ፤
ማነህ ባለተራ?
ምጣድ ያዘጋጀህ - ለእንጀራ ጋገራ?!
እሳት ዳር ቁጭ ብሎ - ፍሙን እየሞቀ
ከትላንት ጥጥ ላይ - የታሪክ ባዘቶ - እየፈለቀቀ
እያጠነጠነ - ሸማ እያጠለቀ
ህዝብ ይኑርልኝ ካልክ - እየፈነደቀ
በሰባራ ምጣድ - ሊጥ አታነካካ
ባለፈው ጋጋሪም - ሙያህን አትለካ
ይልቅ የእልፍኙን ሰው - ሌማቱ እንዲያረካ
በአገር ልክ ጋግር - ከህዝብ ጋር አቡካ!! "ደራሲ ደመቀ ከበደ “አገርና እንጀራ” በሚል ርእስ ስር የገጠመው ግጥም  በዝምታ ጥላ ስር... እህህህህ አስኝቶ ታሪክን ያስቃኛል። 

በስባራ ምጣድ ሊጣቸውን ሳያነካኩት… በህብረት በአገር ልክ የጋገሩትና በአንድነት ከህዝባቸው ጋር ያቦኩት እንጀራቸውን በሰላም እግኝተው እዚህ ደርስዋል። ለእኛ... የኔ አገር፥ ያንተ አገር፥ ያንቺ አገር ለምንባባለው  አንድነቱንና  ህብረቱን ይስጠን። 
የደራሲውም ቀለም ትብራ።

በረከት