27.6.14

መልካም ልደት ለእኔ


ያልደረሳችሁብኝ ድረሱ
የደረስኩባችሁ ተደስቱ
የቀደማችሁኝ ደግሞ መጣሁላችሁ
ይህንን ስል አንድ ሁለት ብለን በምንቆጥረው እድሜ ሳይሆን በአስተያየት በአስተሳስብ በአረማመድ ነው።
ህይወት እኩል አትጀመርም
አንዳችን አንዳችንን ልንቀድም ይገባል።
   አስተያየታችን አስተሳስባችን አረማመዳችን ይለያያል
አስተያየታችን አመለካከታችን ነው…. ነገሮችን እንዴት ነው የምናየው?
አስተሳስባችን የውስጣዊው ባህሪያችን ነው…. ከልቦናችን ምን ይፈልቃል?
አረማመዳችን ደግሞ በእየለቱ የምንኖራት ህይወታችን ናት…. ማንን እንመስላለን?

ስለዚህ አንዳችን አንዳችንን ልንቀድም ይገባል።
 ግን ቀደምንም አልቀደምንም አላማችንና ተስፋችን አንድ ነውና
የቀደመው ወደሃላ የቀረውን ማበረታታትና መጎተት አለበት።

 ሀጢያቴንና። በደሌን ታግሶ በቸርነቱ እዚህ አድርሶኛል በጸጋውም ቆሜአለሁ።
ትናንት የልደቴን ኬክ በላሁ። ባለቤቴ ኬኩን ሲያቀርብልኝ ያለሻማ ነበር። ( ምናልባት ያንን ሁሉ ሻማ ላለመግዛት ወይም ኬኩ በሻማ ብዛት እንዳይጨናነቅም ይሆናል)
ታዲያ አንድ ሻማ አደረገበትና እንደሀገሩ ደንብ make a wish ተባልኩ... ምኞት (wish) ጸሎት ናት? ብዬ ራሴን ጠየቅሁ።
ምኞት ጸሎት ወይም ምልጃ ካልሆነች ምንም ምኞት የለኝም።
 ምኞት ጸሎት ከሆነች ግን ብዙ ጸሎት አለብኝና አንድ ሻማ ብቻ አይበቃኝም...ሆኖም ለአንድ ሻማ አንድ ጸሎት ብቻ ከሆነ… አቤቱ ማረን አልኩና ሻማዬን አጠፋሁ።መዝሙረ ዳዊት 51(50) 
 Psalms 51

በረከት

No comments:

Post a Comment