5.6.14

ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ


"በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥  ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር። " 
ሐዋርያት ሥራ 2፥1-4 

 የጥንቶቹ ስዓሊያን በዓለ ጰራቅሊጦስን እንዲህ አድርገው ስለውታል።  ዘር ማንዘራቸው ይባረክና። 


ጸሎተ ሃይማኖት ሰለመንፈስ ቅዱስ 

"...በመንፈስ ቅዱስ ሰም እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚስጥ ከአብ የሠረፀ፥ ከአብ ከወልድ ጋራ በአንድነት እንሰግድለታለን  እናመሰግነዋለን እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረ ነው።"

መንፈስ ቅዱስን… ሕይወትን የሚስጥ…  ስንል  
«የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወትን ሰጠኝ» ኢዮ 33 4

መንፈስ ቅዱስን… ከአብ የሠረፀ… ስንል    
«እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ ጰራቅሊጦስ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል» ዮሐ 15 26

መንፈስ ቅዱስን… ከአብ ከወልድ ጋራ በአንድነት እንሰግድለታለን  ስንል   
«ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር …» ኢሳ 6 3


እንደ ጥንቱ... እንደ ሐዋሪያቱ እኛም በአንድ ልብ ተስብስበን እናመስግነው ዘንድ አይነ ልቦናችንን ያብራልን፥ አእምሮአችንን ይክፈትልን፥ ውስጣዊውን ባህሪያችንን ይለውጥልን። አሜን

በረከት 

No comments:

Post a Comment