27.6.14

መልካም ልደት ለእኔ


ያልደረሳችሁብኝ ድረሱ
የደረስኩባችሁ ተደስቱ
የቀደማችሁኝ ደግሞ መጣሁላችሁ
ይህንን ስል አንድ ሁለት ብለን በምንቆጥረው እድሜ ሳይሆን በአስተያየት በአስተሳስብ በአረማመድ ነው።
ህይወት እኩል አትጀመርም
አንዳችን አንዳችንን ልንቀድም ይገባል።
   አስተያየታችን አስተሳስባችን አረማመዳችን ይለያያል
አስተያየታችን አመለካከታችን ነው…. ነገሮችን እንዴት ነው የምናየው?
አስተሳስባችን የውስጣዊው ባህሪያችን ነው…. ከልቦናችን ምን ይፈልቃል?
አረማመዳችን ደግሞ በእየለቱ የምንኖራት ህይወታችን ናት…. ማንን እንመስላለን?

ስለዚህ አንዳችን አንዳችንን ልንቀድም ይገባል።
 ግን ቀደምንም አልቀደምንም አላማችንና ተስፋችን አንድ ነውና
የቀደመው ወደሃላ የቀረውን ማበረታታትና መጎተት አለበት።

 ሀጢያቴንና። በደሌን ታግሶ በቸርነቱ እዚህ አድርሶኛል በጸጋውም ቆሜአለሁ።
ትናንት የልደቴን ኬክ በላሁ። ባለቤቴ ኬኩን ሲያቀርብልኝ ያለሻማ ነበር። ( ምናልባት ያንን ሁሉ ሻማ ላለመግዛት ወይም ኬኩ በሻማ ብዛት እንዳይጨናነቅም ይሆናል)
ታዲያ አንድ ሻማ አደረገበትና እንደሀገሩ ደንብ make a wish ተባልኩ... ምኞት (wish) ጸሎት ናት? ብዬ ራሴን ጠየቅሁ።
ምኞት ጸሎት ወይም ምልጃ ካልሆነች ምንም ምኞት የለኝም።
 ምኞት ጸሎት ከሆነች ግን ብዙ ጸሎት አለብኝና አንድ ሻማ ብቻ አይበቃኝም...ሆኖም ለአንድ ሻማ አንድ ጸሎት ብቻ ከሆነ… አቤቱ ማረን አልኩና ሻማዬን አጠፋሁ።መዝሙረ ዳዊት 51(50) 
 Psalms 51

በረከት

23.6.14

ከመለቀቃችን በፊትዛሬ... ስላምን ለማን ስጠሁ?
ዛሬ... የማንን ፊት በፈገግታ አበራሁ?
የማዳንን የተስፋን የፍቅርን ቃል ዛሬ... ለማን ተናገርኩ?
ዛሬ... ቁጣዬንና ቅሬታየን ትቻለሁ? ይቅርታስ አድርጌአለሁ?
ማንን ወደድኩ???
ትናንት አልፋል... ሄዷል... ተለቋል። ዛሬ ግን አሁን ነው። ዛሬ አልተለቀቀችም፥ እኛም አለን፥ ወደላይ አልወጣንም... አልተለቀቅንምና  ከመለቀቃችን በፊት ራሳችንን እንጠይቅ።
ማንን ወደድን?
 

ስላም ለእናንተ ይሁን፥
ቀኞቻችሁ በደስታ በተስፋና በፍቅር ይሞሉ።

በረከት16.6.14

በሎሳንጀለስ ነፃ መንገድ ላይቅዳሜ በሎሳንጀለስ ውስጥ በሚገኘው አንዱ ነፃ መንገድ ላይ ስነዳ፥ በስተቀኝ በኩል ያለው የቢል ቦርድ መልክት፥
“ከሞትክ በኃላ እግዚአብሔርን ታገኛለህ” ይልና የሐዋርያው የጳውሎስ መልእክት ወደ ዕብራውያን 9፥27 ይጠቅሳል። 


ከሞት በኃላ ህይወት አለ ስለዚህም ለፍርድ እንቆማለን። 2ኛ ቆሮንቶስ 5-10 ብንመለከት “መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፥ እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና።” ይላል።
ከሞትን በኃላ እግዚአብሔርን እናገኘዋለንና ዝም ብለን እንደመሰለን መኖር አይገባንም።በምድር ላይ ሳለን የሠራነውን ሁሉ እንቀበላለን። ስለዚህ ተግተን በቅድስና እና በጽድቅ መመላለስ አለብን። አካሄዳችንና ውስጣዊውን ባህሪያችንን በጥንቃቄ መጠበቅ አለብን። 
እንዴት እንደምንኖር መዝሙር 15 እና ወደ ኤፌሶን ሰዎች ከምዕራፍ 4 እሰከ ላይ ያለውን እንመርምር። ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 1914 ላይ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን እንዳለው ሁሉ የአንደበታችን ቃል እንኳን ከልባችን አሳብ ጋር መመሳስል አለበት።
ከሞትን በኃላ እግዚአብሔርን እናገኘዋለንና እንዘጋጅ። 
የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው፤መዝ 90-10  


“ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው” ዕብ 9፥27
ከሞትን በኃላ ለፍርድ እንቆማለንና
ወገኔ ሆይ! ተዘጋጅ
ወገኔ ሆይ! ተዘጋጂ
 እግዚአብሔርን ሰለምናገኘው እንዘጋጅ።

በረከት