ስለ ሂትለር ጭካኔ ያልስማ ፉጡር ያለ አይመስለኝም። ከ German
concentration ካንፕ
ያመለጠውን
Elie Wiesel የጻፈውን እውነተኛ
ታሪክ “Night” የሚለውን መጽሐፍ በሲዲ ስማሁት። ውስጡ አራት ሲዲ ብቻ ነበርና ስእሌን እየሳልኩ ቶሎ
ብዬ ስማሁና ጨረስኩ። አዎን ጭካኔ በምን ይለካል ያስብላል። ዛሬ ተከታዩን “Dawn” ከዚያ በሃላ ደግሞ “Day” የሚለውን እስከምስማ ድረስ
ጓጉቻለሁ።
“Night” የመጽሐፍ መጀመሪያ
ምዕራፍ ላይ ተራኪው…. ከጭካኔው በፊት ስለነበረው ማስጠንቀቂያ እንዲህ ያላል።
…Day after day night after night he want from one Jews
house to the next, telling his story…
He spoke only what he has seen but people not only
refuse to believe his tells, they refuse to listen, some even insinuated he
only wants their pity. He image things, others flatly said that he got mad…
He wiped and pleaded...listen to me that is only
what I asked for you. No money, no pity, listen to me. He kept shouting in
synagogue between prayers in desk and in evening prayers…
Even I didn’t believe him…once I asked him the
question. Why do you want people to believe you so much? In your place I will
not care whether they believe me or not….
He said…. he was saved miraculously, he succeed in
coming back to warn, when there is time but no one listen to him…
ጆሮ ያለው ይስማ እንደሚባለው። እንኳን ከጭካኔ በፊት ሀጢያት
ከመስራት በፊት ማስጠንቀቂያ እንዳለ አለ ኦሪት ዘፍጥረት 4፥7 እናነባለን።
“መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች፤ ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው፥”
ታዲያ ስንቶቻችን ስንቱን ቀይ መብራት ጥስናል? ስንቱን ቁም
የሚለውን ምልክት በዋዛ አልፈናል?
ምናልባት አንዱ ተው ስማኝ እያለ ሰለእኛነታችን ስለወገናችን ስለትውልዳችን ሰለሀገራችን ስለሀይማኖታችን እየጮኸ ይሆናል። ጆሮ
ያለው ይስማ እንደሚባለው እየስማን ነው? ሌላው ቀርቶ ውስጣችን ለራሳችን ትጮኸለች እኮ። እየስማናት ነው?
አንዳንዶች እኛ እንድንስማ ብቻ በተአምር ይተርፋሉ...
ለማንበብ ወይም ለመስማት ለምትፈልጉ ሁሉ መጽሐፉ መልኩ ይህንን ይመስላል
የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ ብሏል ጠቢቡ። እንስማ!
በረከት
No comments:
Post a Comment