15.5.14

የህይወት ውኃ


ትናንትና እና ዛሬ ሙቀቱ ቃጠሎ ነው። 
በዚህ ልብላቤ ግዜ ስውነታችንን ከሙቀት በመጋለት ከሚመጣ ህመም (heatstroke) ለመከላከል ከውኃ
ቀጥሎ ጨውና ሚንራል መተካት ያስፈልገዋል። ስለዚህም በእንደዚህ አይነት ወቅትወይም ግዜ ሙቀት ሙቀት ሆኖ ዘጠና ቤቶችን አልፎ ሲያስቆጥርስውነታችን የራሱን ውኃ
(body fluid) እንዳይቀንስ፥ ቡና አልኮልና ስኳር የበዛባቸውን መጠጥ እንዳንጠጣ ብዙ የህክምናና የጤና ተቃውማት ያስጠነቅቃሉ። እኔም የዛሬዋን ሙቀት ልብልብ ስታደርገኝ 
ሙቀት ሳይኖር አየሩም ሳይለወጥ... ዙሪአቸውና ውስጣቸው ያቃጠላቸው፥ ህይወት ህይወት ኖራ ሳለ... ስሟ ተለውጦባቸው... ህይወት የመንፈስ ጭንቀት፥ ህይወት የነፍሰ ቃጠሎ የሆነችባቸውን እስብኳቸው።
ይረኩና ይቀዘቅዙ ዘንድ የህይወትን ውኃ ይጠጡ ዘንድ በጸሎታችን እናስባቸው።

 ኢየሱስ መልሶ፥ለሴቲቱ እንዲህ አላትእኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ  ዮሐንስ 4 14  


No comments:

Post a Comment