7.4.14

ኒቆዲሞስ Sunday of St. Mary of Egypt

እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም ዮሐ.33


የዐቢይ ጾም ሰባተኛው ሳምንት ወይም እሑድ ኒቆዲሞስ ተብሎ ይጠራል።

ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃና የሸንጎ አማካሪ፣ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለው ሰው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት እጅግ ተማርኮ በሌሊት ወደ እርሱ በመሄድ ይማር ነበር።

ብዙዎች የቤተክርስቲያን አባቶቻችን ኒቆዲሞስን ሌሊት ሌሊት እየሄደ የተማረው አይሁድ ይቃወሙኛል የሚል ፍራቻ ስላደረበት ነው ሲሉን፥ አንዳንዶች አባቶች ደግሞ የሕግ ሰውና መምህር ስለነበረ ካለው የጊዜ እጥረት የተነሳ በሌሊት ይሄድ እንደነበር ይነገግሩናል።
ወጣም ወረደም...  ኒቆዲሞስ በመምህርነቱ ሳይኮራ አለቅነቱን መመኪያ ሳያደርግ፥ በልቦናው ውስጥ ያለውን ጥያቄ ይዞ እውነትን ለመፈለግ በሌሊት ገሠገሠ። ጌታችንም አመጣጡ ለመልካም እንደሆነ አውቆ ለስጋዊ ዕውቀት እጅግ የሚከብደውን ምስጢረ ጥምቀትን ገለጸለት።
የዮሐንስ ወንጌል 313 ስናነብ   
ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በስተቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርስ አይችልም ብሎ ጌታ አስተማረው። አዎን የመንፈስን ነገር ለማወቅ መንፈሳዊ መሆን አለብንና  ኒቆዲሞስ በመጀመሪያ ይህን ምስጢር ለመቀበል አልተቻለውም ነበር  በኋላ ግን ልቦናውን ወደ ሰማያዊው ምስጢር ከፍ ስላደረገ ምስጢሩ ተገለጸለት። 
 በሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምስጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር  የጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውን ገንዞ ለመቅበር በቃ።  
አዎን  የእግዚአብሔር መንግሥት በልጅነት ክብር የምትወረስ ናት።

ስዓሊዎቹም...  ስለማታው ተማሪ እንዲህ ይሉናል


Henry-Ossawa-Tanner, 1899 


 Study, Henry-Ossawa-Tanner ALEXANDER IVANOV, 1850
CRIJN HENDRICKSZ, 1616–1645 

John LaFarge 1880 

በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው፥ ፈተንኸኝ፥ ዐመፅም አልተገኘብኝም።  የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር፥ ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ። መዝ.16፥3


No comments:

Post a Comment