28.4.14

ተስርተን አላለቅንም God’s not done with you


 God is the is a weaver and we are His yarn. He will spin us into fine yarn to become something beautiful to fulfill His good, pleasing and perfect will.
He has a plan for our lives. But as the yarn or clay we need to be willing to let Him make our lives beautiful.
As the word of the Lord came to Jeremiah, 18:1-6  the word of the Lord comes to us: “Like clay in the hand of the potter, so are you in my hand.”
አዎን እግዚአብሔር ሸክላ ስሪ ነው፥ እኛ ጭቃዎቹ። እሱ ሽማኔ እኛ ደግሞ ክሮቹ። ማንም ሆንን ማንም በየግዜውና በየሰዓቱ እግዚአብሔር እንደ ወደደው መልሶ ይስራናል። 
ተደውረን ተፈትለን ክር ሆንን። ልክ እንደ ሸክላ ሠሪው በሽማኔው እጅ ስንገባ ሽማኔው አሳምሮ ይስራናል። ጋቢ፥ ኩታ፥ ነጠላ ወይም ለጥለትና ለጥበብ ያዘጋጀናል።

የሰእሉ መልእክት  
 የሁለቱ ክር ምሳሌ፡ አንዳንዶቻችን ተሰርተነ ያለቅን መስሎን በክርነታችን አብቅተን ተንጋለናል።
በመስራት ላይ ያለው ምሳሌ፡  አንዳንዶቻችን በእግዚአብሔር ቃል እንደገና እየተደወርን ነን።
የጨርቁ ማሳሌ፡ አንዳንዶች ደግሞ በጸሎት በስግደትና በጾም ሰለተጉ… በእግዚአብሔር እጅ ጨርቅ ሆነው ተስርተው፥ ለቃሉ ማደርያ ሆነው፥ ለሌሎቻችን እንደገና ለምንደወረው ጥንካሬ ለመስጠት አቅፈውናል።


 “ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል፥ እንዲህም አለው። ተነሥተህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ውረድ፥ በዚያም ቃሌን አሰማሃለሁ። 
3 ወደ ሸክላ ሠሪው ቤትም ወረድሁ፥ እነሆም፥ ሥራውን በመንኰራኵር ላይ ይሠራ ነበር። 
4 ከጭቃም ይሠራው የነበረ ዕቃ በሸክላ ሠሪው እጅ ተበላሸ፥ ሸክላ ሠሪውም እንደ ወደደ መልሶ ሌላ ዕቃ አድርጎ ሠራው። 
5 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 
6 የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ዘንድ መሥራት አይቻለኝምንእነሆ፥ ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፥ እንዲሁ እናንተ በእኔ እንጅ አላችሁ።
ኤርምያስ 18:1-6   እነሆ፥ ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፥ እንዲሁ እናንተ በእኔ እንጅ አላችሁለሚለን እግዚአብሔር ይስራን ዘንድ እንዘጋጅ። ተስርተን አላለቅንምና።

በረከት

No comments:

Post a Comment