26.4.14

Get Out!... ውጡ!


አዳምንም አስወጣው፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ። ዘፍ፡3-24
 ሁላችንም በአዳምና በሔዋን ኃጢአት ምክንያት በመርገመ ሥጋ በመርገመ ነፍስ ተይዘን ነበር። ከመርገመ ሥጋ፥ ከመርገመ ነፍስ ነፃ  እንሆን ዘንድ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ። 
ስለመተላለፋችንና ስለበደላችን ሲል ሞተ። ያጣነውን ልጅነት ሊመልስልንከተቀማነው ርስት ሊያስገባን…   አዲስ ሕይወትና ምግብን ለመስጠት ሞተ።
ሞትን ድል አድርጎ በክብር ወደ ሰማየ ሰማያት አረገ። በዚህም ምክኒያት ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ ድል መንሳትህስ ወዴት አለ? ተባለ


ስዓሊው Heinrich Kley ገነት ደጃፍ ላይ " ፎቶ ማንሳት የተከለከለ ነው" የሚል ጽሁፍ ለጠፈ።  
ፎቶ ማንሳት ብቻ ሳይሆን 
በትንሣኤውም ታላቅ ጸጋ አገኘን፥ከሞት ወደ ሕይወት፥ ከሃሳር ወደ ክብር፥   ከሲኦል ወደ ገነት ተሽጋገርን።

  መልካም ዳግመ ትንሳኤ
በረከት 

No comments:

Post a Comment