28.4.14

ተስርተን አላለቅንም God’s not done with you


 God is the is a weaver and we are His yarn. He will spin us into fine yarn to become something beautiful to fulfill His good, pleasing and perfect will.
He has a plan for our lives. But as the yarn or clay we need to be willing to let Him make our lives beautiful.
As the word of the Lord came to Jeremiah, 18:1-6  the word of the Lord comes to us: “Like clay in the hand of the potter, so are you in my hand.”
አዎን እግዚአብሔር ሸክላ ስሪ ነው፥ እኛ ጭቃዎቹ። እሱ ሽማኔ እኛ ደግሞ ክሮቹ። ማንም ሆንን ማንም በየግዜውና በየሰዓቱ እግዚአብሔር እንደ ወደደው መልሶ ይስራናል። 
ተደውረን ተፈትለን ክር ሆንን። ልክ እንደ ሸክላ ሠሪው በሽማኔው እጅ ስንገባ ሽማኔው አሳምሮ ይስራናል። ጋቢ፥ ኩታ፥ ነጠላ ወይም ለጥለትና ለጥበብ ያዘጋጀናል።

የሰእሉ መልእክት  
 የሁለቱ ክር ምሳሌ፡ አንዳንዶቻችን ተሰርተነ ያለቅን መስሎን በክርነታችን አብቅተን ተንጋለናል።
በመስራት ላይ ያለው ምሳሌ፡  አንዳንዶቻችን በእግዚአብሔር ቃል እንደገና እየተደወርን ነን።
የጨርቁ ማሳሌ፡ አንዳንዶች ደግሞ በጸሎት በስግደትና በጾም ሰለተጉ… በእግዚአብሔር እጅ ጨርቅ ሆነው ተስርተው፥ ለቃሉ ማደርያ ሆነው፥ ለሌሎቻችን እንደገና ለምንደወረው ጥንካሬ ለመስጠት አቅፈውናል።


 “ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል፥ እንዲህም አለው። ተነሥተህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ውረድ፥ በዚያም ቃሌን አሰማሃለሁ። 
3 ወደ ሸክላ ሠሪው ቤትም ወረድሁ፥ እነሆም፥ ሥራውን በመንኰራኵር ላይ ይሠራ ነበር። 
4 ከጭቃም ይሠራው የነበረ ዕቃ በሸክላ ሠሪው እጅ ተበላሸ፥ ሸክላ ሠሪውም እንደ ወደደ መልሶ ሌላ ዕቃ አድርጎ ሠራው። 
5 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። 
6 የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ዘንድ መሥራት አይቻለኝምንእነሆ፥ ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፥ እንዲሁ እናንተ በእኔ እንጅ አላችሁ።
ኤርምያስ 18:1-6   እነሆ፥ ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፥ እንዲሁ እናንተ በእኔ እንጅ አላችሁለሚለን እግዚአብሔር ይስራን ዘንድ እንዘጋጅ። ተስርተን አላለቅንምና።

በረከት

26.4.14

Get Out!... ውጡ!


አዳምንም አስወጣው፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ። ዘፍ፡3-24
 ሁላችንም በአዳምና በሔዋን ኃጢአት ምክንያት በመርገመ ሥጋ በመርገመ ነፍስ ተይዘን ነበር። ከመርገመ ሥጋ፥ ከመርገመ ነፍስ ነፃ  እንሆን ዘንድ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ። 
ስለመተላለፋችንና ስለበደላችን ሲል ሞተ። ያጣነውን ልጅነት ሊመልስልንከተቀማነው ርስት ሊያስገባን…   አዲስ ሕይወትና ምግብን ለመስጠት ሞተ።
ሞትን ድል አድርጎ በክብር ወደ ሰማየ ሰማያት አረገ። በዚህም ምክኒያት ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ ድል መንሳትህስ ወዴት አለ? ተባለ


ስዓሊው Heinrich Kley ገነት ደጃፍ ላይ " ፎቶ ማንሳት የተከለከለ ነው" የሚል ጽሁፍ ለጠፈ።  
ፎቶ ማንሳት ብቻ ሳይሆን 
በትንሣኤውም ታላቅ ጸጋ አገኘን፥ከሞት ወደ ሕይወት፥ ከሃሳር ወደ ክብር፥   ከሲኦል ወደ ገነት ተሽጋገርን።

  መልካም ዳግመ ትንሳኤ
በረከት 

19.4.14

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ"ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ

መልካም ፋሲካ
  
በረከት

18.4.14

ስቅለት Good Friday
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ 
የዓለም ሁሉ መድኃኒት፥ 
ዓለምን ለማዳን ተገርፎ፣ተዋርዶ፣ተሰድቦ፣የሃጢአተኞች ምራቅ ተተፍቶበት፣መስቀል ተሸክሞ፥ ቀራንዮ ወይም ጎልጎታ ተራራ ላይ ወጥቶ፣ እጆቹና እግሮቹ ተቸንክረው በዕለተ ዓርብ ቀትር ላይ ከምድር ከፍ ከሰማይ ዝቅ ብሎ ተሰቀለ። 
የጌታችን የመዳህኒታችን የእየሱስ ክርስቶስን ውለታ እያሰብን፥ በንስሓ ታጥበን፥ ሥጋውንና ደሙን ለመቀበል ከእርሱ ጋር በአንድነትና በኅብረት እንድንኖር ያበቃን ዘንድ፥የምንማጸንበት፤ ደጅ የምንጠናበት፤ቀን ይሁንልን።

አሜን 

12.4.14

bereketdecor: የዐቢይ ጾም ስምንተኛው እሑድ... ሆሳዕና

bereketdecor: የዐቢይ ጾም ስምንተኛው እሑድ... ሆሳዕና: "በጌታ ስም ሆኖ መጥቶልናልና ቡሩክ ወልደ ዳዊት ይድረስው ምስጋና ...  በአህያ ላይ ሆኖ የስራዊት ጌታ ገባ እየሩሳሌም በታላቅ ደሰታ ዘንባባውን ይዘን እንዘምር በእልልታ ሆሳዕና ለወልደ ዳዊት...

11.4.14

የጾም ፓስታ Vegan Pasta
1 cup of cooked Chickpeas (Garbanzo beans) 

If you wish…remove the skins...
የተቀቀለ 1 ስኒ ሽንብራ...ከፈለጉ ቆዳውን ይለዩ... Soak 1/3 cup dried porcini mushrooms in 1 cup of hot water for 10 minutes...
የደረቀውን ማሽሩም በ1 ስኒ የሞቀ ውሀ ለ10 ደቂቃ ይዘፍዝፉ...Strain through sieve and set both the mushrooms and liquid aside…
የተዘፈዘፈውን ማሽሩምና ውሀውን ይለዪና ያስቀምጡ... Heat the oil over in a large saute pan over medium heat….add chopped yellow onion and sauté …about 3 minutes…
ሽንኩርቱን በዘይት ይጥበሱ...

add chickpeas and sauté until lightly browned….
ሽንብራውን ይጨምሩና ጠበስ ያድርጉት... እንዳያር ግን ተጠንቀቁ 


add garlic and rosemary and sauté, about 2 minutes…
ነጭ ሽንኩርትና የጥብስ ቅጠሉን ይጨምሩ ከሁለት ደቂቃ በሃላ... 

add porcini mushrooms and Fresh mushrooms and cook…
የተዘፈዘፈውንና እርጥብ ማሽሩም ይጨምሩ ትንሸ ካቁላሉት በሃላ... 

when they release their liquid add the wine….after 1 minutes add the reserved mushroom liquid….
ዋይኑን ይጨምሩ ከአንድ ደቂቃ በሃላ የማሽሩምን ውሀ ይጨምሩ... 


Cook until the flavors have blended, about 10 minutes.
Remove from the heat, season to taste with salt and pepper.

ከአሰር ደቂቃ በሃላ፥ ጨውና ቁንዶ በርበሬውን ያስተካክሉና ያውጡ 
Ingredients:
3 tablespoons Olive oil
1 yellow onion, chopped
4 Garlic, minced
1 cup of cooked Chickpeas (Garbanzo beans)
1 spring fresh rosemary
1/3-cup Dried porcini mushrooms
Fresh mushrooms about 2 cups
½ cup dry red wine
Salt and black pepper
Rigatoni pasta 
fresh parsley, to garnish


አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች:

3 የሾርባ ማንኪያ የወይራ ዘይት

 1 ሽንኩርት
3 ነጭ ሽንኩርት
 1 ስኒ የተቀቀለ ሽንብራ
1 ትንሽ ግንድ የጥብስ ቅጠል
1/3 ስኒ የደረቀ ማሽሩም
2 ስኒ እርጥብ (fresh) ማሽሩም
ግማሽ ስኒ ቀይ ዋይን
ጨውና ቁንዶ በርበሬ
ፓስታWhen you have eaten and you are full… then you shall bless the Lord
Deuteronomy 8:11

ከበላህና ከጠገብህ በኃላ … አምላክህን እግዚአብሔርን አስብ። 
ኦሪት ዘዳግም 8:11በረከት