31.3.14

ታማኝ አገልጋይ Sunday of St. John Climacusየዐቢይ ጾም ስድስተኛው እሑድ ገብር ኄር ወይም ታማኝ አገልጋይ ተብሎ ተሰይሟል። ሰያሜውን የሰጠውም ኢትዮጵያዊ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በማቴ.2514-25 የተገለጸው ታሪክ  በማስመልከት ነው።

....አንድ ባዕለ ጸጋ ሰው ባሪያዎችን ጠርቶ ለአንዱ አምስት መክሊት፥ ለአንዱ ሁለት፥ ለአንዱ ደግሞ፥ አንድ መክሊት ሰጠና ወደሩቅ አገር ሄደ… አምስት መክሊት የተቀበለውም ወጥቶ ወርዶ ሌላ አምስት አትርፎ አስር አደረገ። ሁለት የተቀበለውም አትርፎ አራት አደረገ። አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ መሬቱን ቆፍሮ የጌታውን መክሊት ቀበራት…. ከብዙ ጊዜ በኋላ ጌታቸው መጣ…..
ማቴ.25፥14-25

አባቶቻችን የዚህን ምሳሌያዊ ታሪክ ምስጢር ሲያስተምሩ፥ የአገልጋዮቹ ጌታ...  የእግዚአብሔር ምሳሌ ሲሆን፥  ሦስቱ አገልጋዮች ደግሞ በተለያየ ደረጃ ያሉ ምዕመናንን እንደሚወክሉና መክሊት የተባለው ልዩ ልዩ የሕይወት አገልግሎት እንጂ የሙያ እንዳልሆነ ያስተምሩናል።

እግዚአብሔር እያንዳንዳችን በሃይማኖት ሆነን የምናፈራውን ፍሬ ይፈልጋል።
ታማኝነት፥ ትእግሥትነት (ታጋሽነት)፥ ትሑትነት፥ ሰላማዊነት የመሳሰሉት  የምዕመናን የሕይወት አገልግሎቶች መክሊቶች ናቸው። እነዚህን ካላሳደግናቸው የጌታውን መክሊት እንደቀበራት ሁሉ … ጸጋችንን ቀበርን ማለት ነውና። 
ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዳቅማችን የተስጠንን ይህንን ጸጋችን… 
በብዙ ለማትረፍ የምንሮጥ አገልጋዮች ነን?
ወይስ 
መከራ ቢመጣብኝስ ብለን  መክሊታችን የምንቀብር ነን?
ራሳችንን እንጠይቅ… እንጠየቅበታለንና
   
ስዓሊዎቹም... በተለያየ መልኩ እንዲህ ይሉናል…
እግዚአብሔር በሰጠን ጸጋ መጠን እንድንስራና ጸጋውን እንዲያበዛልን እንለምነው።

አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥
ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው
በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አወራሁ።  መዝ. 39÷8

No comments:

Post a Comment