10.3.14

ምኩራብ.. Sunday of Orthodoxy

Carl Heinrich Bloch, 1875

ጌታ በምኩራብ ገብቶ… የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉ… ቤቴ የጸሎት ቤት ነው… ብሎ በጅራፍ መንጋዎቹን ከነጋዴዎቻቸው ጋር ከቤተመቅደስ እንዳስወጣና የሃይማኖትን ቃል እንዳስተማረ መታሰቢያ ሆኖ  የሚዘመርበት ሶስተኛው የጾም ሳምንት ምኩራብ ይባላል።

በዚህ ሳምንት የምናስበውን... ምኩራብ... ብዙ ስዓሊያን በተለያየ መልኩ ስለውታል። ጌታ ቤተ መቅደሱን ለማስከበሩ መታሰቢያነት የተሳሉት እንዚህን ስእላት ስመለከት…ዛሬም የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ የሆነውን ቤተ መቅደሶቻችን አስብኳቸው።…

James Tissot, between 1886 and 1894


ከሁሉም ይበልጥ እኛነታችንን አስመለከተኝ።
ሁላችንም የእግዚአብሔር ክብር መገለጫዎች ነን። ሁላችንም እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፥ በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ደም የተገነባን ነነና… ታዲያ ማንም ይህን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል የሚለውን ቃል አስብኩና… እግዚአብሔር ወደ እኛ ቤተ መቅደስ ወደተመሰለው ልቦናና ሰውነት ሲመለክት ምን ያገኛል? ምን ያያል?  ምን እተከናወነበት ነው? እንደ ምኩራቡ የሁሉም ገበያ… የኃጢአት ገበያ እንዳይሆን ብዬ ራሴን ጠየቅሁ…አቤቱ ማረን…  ወደእርሱ በንስሐ እንቅረብ።

El Greco, 1568


Valentin de Boulogne between 1620 and 1625


Carl Heinrich Bloch, 1875


El Greco, 1571


Giovanni Benedetto Castiglione, 1625-50


El Greco, 1609

የቤትህ ቅናት በልቶኛል የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ላይ ወደቀ ነፍሴን በጾም አስመረርኳት
መዝ 689

Passion for your house has consumed me,
and the insults of those who insult you have fallen on me.When wept and humbled my soul with fasting,
it became my reproach
Psalm 69:9
No comments:

Post a Comment