8.3.14

የሽንብራ ልጥልጥ Hummus

በእንጀራ... በቂጣ...  በሳንድውች ውስጥ ወይም  በስላጣ... እንደ አመሎት.. እንደ አምሮቶት... የሽንብራ ልጥልጥ ለጤናዎ 

የበሰለው ሱፍ… በምግብ መፍጫ በደንብ…መምታት...የተመታውን የሱፍ ውሀ ማጥለል

Blend..Cook Sunflower seeds..  until all the seeds are crushed..place strainer over bowl to collect the sunflower liquids...
በምግብ መፍጫ ውስጥ…በሙሉ ማደባለቅና ቀስ እያሉ መፍጨት..
Combine everything in a food processor and process until…

የሽንብራ ልጥልጥ (Hummus)

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች:

3 ስኒ የተቀቀለ ሽንብራ
2 ስኒ የሱፍ ውሀ
3 ነጭ ሽንኩርት
የአንድ ሎሚ ጭማቂ
½ የአንድ የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ኩምን (cumin)
½ የአንድ የሻይ ማንኪያ የተፈጨ እርድ
1/3 ስኒ (5 የሾርባ ማንኪያ) የወይራ ዘይት፥
ጨውና ቁንዶ በርበሬ
(ትንሽ ብትን በርበሬና በደቃቁ የተከታተፈ የሾርባ ቅጠል parsley ለማሳመርያ ያህል)   

አዘገጃጀት
  
1) ሽንብራ መቀቀል፤ ከፍ ባለ ኀድጓዳ ሳህን ውስጥ የታጠብውን ሽንብራ በቀዝቃዛ ውሀ ዘፍዝፎ ማሳደር። በማግስቱ፥ የተዘፈዘፈውን ሽንብራ አለቅልቆ፥ ከፍ ባለ መቀቀያ ድስት ውስጥ ከበቂ ውሀ ጋር አድርጎ ለአንድ ሰዓት ያህል ወይም እስኪበስል ድረስ መቀቀል። 3 ስኒ የተቀቀለ ሽንብራ
  2) ሱፍ መቀቀል የተለቀመውንና የታጠበውን ሱፍ መቀቀያ ድስት ውስጥ ከበቂ ውሀ ጋር አድርጎ ለ 25 ደቂቃ ያህል ወይም እስኪበስል ድረስ መቀቀል። የበሰለው ሱፍ እስኪቀዘቅዝ ለአንድ 15 ደቂቃ መተው። ከዝቀዝ ያለውን ሱፍ ከሁለት ስኒ ውሀ ጋር በምግብ መፍጫ በደንብ መፍጨት ወይም መምታት። የተመታውን የሱፍ ውሀ ማጥለል። 2 ስኒ የሱፍ ውሀ

   3) ሽንብራ ልጥልጥ መስራት፤  ከወይራ ዘይት በስተቀር በምግብ መፍጫ ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን (3 ስኒ የተቀቀለ ሽንብራ ፥2 ስኒ የሱፍ ውሀ፥ነጭ ሽንኩርት፥ የአንድ ሎሚ ጭማቂ፥ ኩምንና እርዱን) በሙሉ ማደባለቅና ቀስ እያሉ መፍጨት። ወይራ ዘይቱን እየጨመሩ በደንብ ልንቅጥ እስከሚል መፍጨት። የጨውን ቃና አስተካክሎ ከጠርሙስ በተሰራ እቃ ገልብጦ ማቀዝቀዣ ውስጥ ማስቀመጥ። ሲያቀርቡት ለማሳመርያ ያህል ትንሽ በርበሬና በደቃቁ የተከታተፈ የሾርባ ቅጠል በተን ማድረግ።Hummus (Yeshimbra Deleh) 

Ingredients

3 cups cooked,drained chickpeas
2 cups of sunflower liquid
3 cloves garlic, peeled
Juice of 1 lemon, plus more as needed
½ tsp ground cumin
½  tsp ground tumeric
1/3 cup (about 5 Tablespoons) extra-virgin olive oil,
Salt and freshly ground black pepper to taste

(Paprika for sprinkling and Chopped fresh parsley leaves for garnish)

Directions
1) Cook Chickpeas: Place chickpeas in a large bowl and cover completely with cold water. soak them overnight. Once chickpeas have soaked, drain and the water and rinse.  Transfer to a large cooking pot and Bring to a boil, then reduce to a simmer and cook, covered, for one hour, or until soft.

(Cooked chickpeas can keep covered in the refrigerator for up to three days.)

2) Cook Ethiopian Sunflower Seeds (Suf): Sort through the sunflower seeds and wash them in cold water. In a cooking pot, cover the sunflower seeds in cold water; boil for 25 minutes or until soft. Allow to cool for 15 minutes.
Drain and place the cooked sunflower seeds in a food processor; add two cups of cold water; blend until all the seeds are crushed.
place strainer over bowl to collect the sunflower liquids; discard the sunflower sediments.
3) Make Hummus: Using a food processor, pulse the chick peas, sunflower liquids, lemon, garlic cloves, cumin and tumeric. While the food processor is running, slowly pour in the olive oil. Taste and adjust the seasoning.  To serve, transfer the hummus to a bowl and sprinkled with a bit of paprika and some parsley. If desired…drizzle with additional olive oil ከበላህና ከጠገብህ በኃላ … አምላክህን እግዚአብሔርን አስብ። 
ኦሪት ዘዳግም 8:11

When you have eaten and you are full… then you shall bless the Lord
Deuteronomy 8:11

1 comment:

  1. Thank you bereket

    Delicious receipies

    yeshi

    ReplyDelete