29.3.14

5.1 መሬት መንቀጥቀጥ


ከምሽቱ 9:05pm አካባቢ ማለትም (ከአንድ ሶስት ስዓት በፊት) ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ መጣ።
የቆምኩባት መሬት ስትንጛጛና ስትንቀጠቀጥ ለትንሽ ስከንድ ያህል መብራት ጠፉ፥እኔም  ተደናገጥኩ ልቤም በፍጥነት መታ። ወደመውጫው በር ስር ቆምኩ።
ቤቱም ተወዛወዘ፥ አንዳንድ እቃዎቻችን ከተቀመጡበት ወደቁ።
ትንፋሼም የአምላኳን ስም ጠራች
እግዚኦ አቤቱ ማረኝ… እግዚኦ አቤቱ ማረን… አልኩ
ተዘጋጂቻለሁን? አረ ቆይ…
እግዚኦ አቤቱ ማረን….
የባትሪ (የፍላሽ) መብራት ፈለግሁና ከአጠገባችን አስቀመጥኩ።
ከትንሽ ደቂቃ በሃላ መሬቷ እንደገና ሽው ሽው አለች።
አቤቱ ህዝብህን አድን… አቤቱ ይቅር በለን….
ያለሁበት አካባቢ ከመሬቱ መንቀጥቀጥ ከጀመረበት ቦታ La Habra ምናልባት ሁለት ማይል እርቀት እንደማይሞላና የመሬቱ መንቀጥቀጡም ፍጥነት 5.1 መሆኑን ዜናዎቻችን አስታወቁን።
እግዚኦ አቤቱ ማረን…
እኔም የወዳደቁትን እቃዎች ማነሳሳት ጀመርኩ። የራስጌ መብራቱ እንደበራ መሬት ላይ ወድቋል። ለትንሽ ደቂቃ ቆም አልኩና አስተዋልኩ….
የራስጌ መብራቱን ከማንሳቴ በፊት ፎቶ አነሳሁት።


እንደበራ መሬት ላይ ወድቋል….
ብዙዎቻችን ገና ጉልበቶቻችን አልከዱንም፥ እስትንፋሾቻችን የፈጣሪን እፍታን ብርሀንን  ተጎናፅፈዋል… ታድያ 

በርተን መሬት ለመሬት...  በርተን መንጋለል ብቻ... ብርሀናችን ለአልጋ ስር... እንዳይሆን... እንደበራን እንዳንወድቅ ፈራሁ።    

  እኔም እንደበራሁ እንዳልወድቅ በፅሎታችሁ አስቡኝ። 

ከዚህ ይበልጥ መሬቱ መንቀጥቀጥ እንዳይመጣብን እባካችሁን በፅሎቶቻችሁ አስቡን።

በረከት 

3 comments:

 1. አይዞሽ በረከት ምንግዜም እግዚአብሔር ከመሬት መንቀጥቀጥ በሐላ በሲና ተራራ ለሙሴ እንዳናገረው

  ድምፁን ሊያሰማን ይሆናል፡፡

  ሠላም ለኪ !

  ወላዲተ አምላክ ትጠብቃችሁ

  የሺ

  ReplyDelete
 2. berche Ayzoshe!!!

  ReplyDelete
 3. ብዙዎቻችን ገና ጉልበቶቻችን አልከዱንም፥ እስትንፋሾቻችን የፈጣሪን እፍታን ብርሀንን ተጎናፅፈዋል… ታድያ
  በርተን መሬት ለመሬት... በርተን መንጋለል ብቻ... ብርሀናችን ለአልጋ ስር... እንዳይሆን... እንደበራን እንዳንወድቅ ፈራሁ።

  ReplyDelete