31.3.14

ታማኝ አገልጋይ Sunday of St. John Climacusየዐቢይ ጾም ስድስተኛው እሑድ ገብር ኄር ወይም ታማኝ አገልጋይ ተብሎ ተሰይሟል። ሰያሜውን የሰጠውም ኢትዮጵያዊ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በማቴ.2514-25 የተገለጸው ታሪክ  በማስመልከት ነው።

....አንድ ባዕለ ጸጋ ሰው ባሪያዎችን ጠርቶ ለአንዱ አምስት መክሊት፥ ለአንዱ ሁለት፥ ለአንዱ ደግሞ፥ አንድ መክሊት ሰጠና ወደሩቅ አገር ሄደ… አምስት መክሊት የተቀበለውም ወጥቶ ወርዶ ሌላ አምስት አትርፎ አስር አደረገ። ሁለት የተቀበለውም አትርፎ አራት አደረገ። አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ መሬቱን ቆፍሮ የጌታውን መክሊት ቀበራት…. ከብዙ ጊዜ በኋላ ጌታቸው መጣ…..
ማቴ.25፥14-25

አባቶቻችን የዚህን ምሳሌያዊ ታሪክ ምስጢር ሲያስተምሩ፥ የአገልጋዮቹ ጌታ...  የእግዚአብሔር ምሳሌ ሲሆን፥  ሦስቱ አገልጋዮች ደግሞ በተለያየ ደረጃ ያሉ ምዕመናንን እንደሚወክሉና መክሊት የተባለው ልዩ ልዩ የሕይወት አገልግሎት እንጂ የሙያ እንዳልሆነ ያስተምሩናል።

እግዚአብሔር እያንዳንዳችን በሃይማኖት ሆነን የምናፈራውን ፍሬ ይፈልጋል።
ታማኝነት፥ ትእግሥትነት (ታጋሽነት)፥ ትሑትነት፥ ሰላማዊነት የመሳሰሉት  የምዕመናን የሕይወት አገልግሎቶች መክሊቶች ናቸው። እነዚህን ካላሳደግናቸው የጌታውን መክሊት እንደቀበራት ሁሉ … ጸጋችንን ቀበርን ማለት ነውና። 
ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዳቅማችን የተስጠንን ይህንን ጸጋችን… 
በብዙ ለማትረፍ የምንሮጥ አገልጋዮች ነን?
ወይስ 
መከራ ቢመጣብኝስ ብለን  መክሊታችን የምንቀብር ነን?
ራሳችንን እንጠይቅ… እንጠየቅበታለንና
   
ስዓሊዎቹም... በተለያየ መልኩ እንዲህ ይሉናል…
እግዚአብሔር በሰጠን ጸጋ መጠን እንድንስራና ጸጋውን እንዲያበዛልን እንለምነው።

አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥
ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው
በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አወራሁ።  መዝ. 39÷8

29.3.14

5.1 መሬት መንቀጥቀጥ


ከምሽቱ 9:05pm አካባቢ ማለትም (ከአንድ ሶስት ስዓት በፊት) ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ መጣ።
የቆምኩባት መሬት ስትንጛጛና ስትንቀጠቀጥ ለትንሽ ስከንድ ያህል መብራት ጠፉ፥እኔም  ተደናገጥኩ ልቤም በፍጥነት መታ። ወደመውጫው በር ስር ቆምኩ።
ቤቱም ተወዛወዘ፥ አንዳንድ እቃዎቻችን ከተቀመጡበት ወደቁ።
ትንፋሼም የአምላኳን ስም ጠራች
እግዚኦ አቤቱ ማረኝ… እግዚኦ አቤቱ ማረን… አልኩ
ተዘጋጂቻለሁን? አረ ቆይ…
እግዚኦ አቤቱ ማረን….
የባትሪ (የፍላሽ) መብራት ፈለግሁና ከአጠገባችን አስቀመጥኩ።
ከትንሽ ደቂቃ በሃላ መሬቷ እንደገና ሽው ሽው አለች።
አቤቱ ህዝብህን አድን… አቤቱ ይቅር በለን….
ያለሁበት አካባቢ ከመሬቱ መንቀጥቀጥ ከጀመረበት ቦታ La Habra ምናልባት ሁለት ማይል እርቀት እንደማይሞላና የመሬቱ መንቀጥቀጡም ፍጥነት 5.1 መሆኑን ዜናዎቻችን አስታወቁን።
እግዚኦ አቤቱ ማረን…
እኔም የወዳደቁትን እቃዎች ማነሳሳት ጀመርኩ። የራስጌ መብራቱ እንደበራ መሬት ላይ ወድቋል። ለትንሽ ደቂቃ ቆም አልኩና አስተዋልኩ….
የራስጌ መብራቱን ከማንሳቴ በፊት ፎቶ አነሳሁት።


እንደበራ መሬት ላይ ወድቋል….
ብዙዎቻችን ገና ጉልበቶቻችን አልከዱንም፥ እስትንፋሾቻችን የፈጣሪን እፍታን ብርሀንን  ተጎናፅፈዋል… ታድያ 

በርተን መሬት ለመሬት...  በርተን መንጋለል ብቻ... ብርሀናችን ለአልጋ ስር... እንዳይሆን... እንደበራን እንዳንወድቅ ፈራሁ።    

  እኔም እንደበራሁ እንዳልወድቅ በፅሎታችሁ አስቡኝ። 

ከዚህ ይበልጥ መሬቱ መንቀጥቀጥ እንዳይመጣብን እባካችሁን በፅሎቶቻችሁ አስቡን።

በረከት 

24.3.14

ደብረ ዘይት & Sunday of the Holy Cross


የዐቢይ ጾም አምስተኛ እሑድ ደብረ ዘይት ተብሎ ይጠራል። ጌታችን ስለ ዳግም መምጣቱ ምልክትና ስለ ዓለም መጨረሻ የተናገረው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ በመሆኑ፥ ይህንን ዕለት ቅዱስ ያሬድ ደብረ ዘይት ብሎ ሰይሞታል።
በዕለቱም የቀረበው የቅዱስ ያሬድ ዝማሬ እንዲህ የሚል ነው…

“የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ የሰማይና የምድር ሠራዊት ሁሉ ይነቃነቃል። ያን ጊዜ በምድር የሚኖሩ ኃጢአተኞች ሁሉ ያለቅሳሉ። ጌታችንም ከአእላፍ መላእክት ጋር በትእዛዙና በቃሉ መሠረት ከሰማይ ወደ ምድር ይወርዳል። የእግዚአብሔር መለከትም ይሰማል። በዚያች ሰዓት እርሱ ያድነን። እርሱ የሕይወት ባለቤት ነውና።”

ይህንን ዝማሬ ቅዱስ ያሬድ የዘመረው… ማቴዎስ 24:3 ን ነው።

አዎን! ጌታችን በእርግጥ ዳግም ይመጣል።
በእርግጥም ዳግም፥ በድንገት፥ በግልጥና በክብር እኛን ለመውሰድ ይመጣል።

እንዴት ነው የምንጠብቀው???... ብላ ቤተክርሰቲያናችን ዋናውን ህይወታዊው ጥያቄ ታቀርብልናለች። መልሱንም…
 ነቅተን... 1ተስ 5: 4-11
ልብሳችንን ለብሰን... ራእይ 16:15
መብራታችንን ይዘን... ማቴ 25:6 
እንድንጠብቀው ትናንት አስተማረችን።

የተስፋችን ፍጻሜ ነውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ተግተን እንጠብቅ።
ስዓሊዎቹም... በተለያየ መልኩ እንዲህ ይሉናል…

Gustave Dore, Fineartnorthamerica.com


Orthodox Christian Church Icon
Hans Memling, 1466-1473. National Museum, Gdańsk


Michelangelo, 1536-1541  Sistine Chapel ceiling


William Blake ,1808, Ink and watercolour


አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና 

ራእይ 22:20

He who testifies to these things says, “Surely I am coming soon.” Amen. Come, Lord Jesus!
Revelation 22:20


20.3.14

የጾም ሳንዱች vegan sandwich2 Red bell peppers
Preheat the oven to 400° F / 200 °C
Cut out the stem of each pepper and cut it in half lengthwise. Place the peppers on pan and place in the oven for 30 to 40 minutes, until the skins are completely roasted...

ምድጃውን 400° F / 200 °C ያሙቁ፥ በቁመቱ የተቆራረጠውን ወፍራሙ ቀዩን ቃርያ በምድጃ ውስጥ 30 እስከ 40 ደቂቃ ያህል ይጥበሱት... 2 tablespoons extra virgin olive oil mix with 1minced garlic and ½ spoon pepper flake and season with salt. Whisk all ingredients together in a small bowl....
2 የሾርባ ማንኪያ ዘይት፥ 1 የተፈጨ ነጭ ሽንኩርትና ግማሽ የሻይ ማንኪያ የበርበሬ ፍሬ፥ከትንሽ ጨው ጋር ያደባልቁ... Preheat the oven to 400° F / 200 °C. Line a baking sheet with parchment paper or lightly grease.
Slice the eggplant, Brush each piece with
 olive oil, garlic and pepper flake dressing. Roast in the preheated oven until softened and golden brown, 25 to 30 minutes....
 የነጭ ሸንኩርት እርጥብ ቅመም የተቆራረጠውን ገበርጃን ይቀቡና የሞቀው ምድጃ ውስጥ 25 እሰከ 30 ደቂቃ ያህል ይጥበሱት... 
2 lbs. spinach, 1 Tbsp. olive oil and Salt. Heat a large skillet. Add the olive oil and Quickly add spinach and cook, stirring, until spinach is wilted. Season with salt and pepper and toss again....
በመጥበሻ ላይ ጎመኑን ከትንሽ ዘይት ጋር ለብ ለብ ድርጉ...Ingredients

Olive tapenade spread Click here for Tapenade Recipe
http://bereketdecor.blogspot.com/2013/08/blog-post_29.html
Roasted red bell pepper
Roasted eggplant
Sauteed spinach
Your choice of any sliced bread
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች 

የወይራ ፍሬ ድልህ (tapenade ) ወይራ ፍሬ ድልህ አስራር
http://bereketdecor.blogspot.com/2013/08/blog-post_29.html
በምድጃ ውስጥ የተጠበስ ወፍራሙ ቀይ ቃርያ  (Roasted red bell pepper)
በምድጃ ውስጥ የተጠበስ ገበርጃን (Roasted eggplant)
በመጥበሻ ላይ ለብ ለብ ያለ ጎመን (Sauteed spinach)
የሚወዱት አይነት ዳቦ


When you have eaten and you are full… then you shall bless the Lord
Deuteronomy 8:11

ከበላህና ከጠገብህ በኃላአምላክህን እግዚአብሔርን አስብ። 
ኦሪት ዘዳግም 8:11