20.2.14

የመፅሐፍ ባልንጀራ
ደራሲው ቃላቶችን ስብስቦ ስዕል ሲሆኑለት... በጋዜጣ፥ በመፅሔት ወይም በመፅሐፍ ያካፍለናል።
ይህንን ስዕል ላለመመልከት አንገታችንን ያዞርን ብዙ ብንሆንም፤ ደራሲው ብዕሩን ሳያደርቅ የተዋቡ መፅሐፍቶችን አስረክቦናል።

“አንድ መጽሐፍን ወደ ቤታችን ይዘን ስንገባ አንድ ባልንጀራ ይዘን ወደ ቤታችን መግባታችን ነው” ደራሲ ዲያቆን አሽናፊ እንዳሉት፥ ቤታችንን በብዙ ባልንጀራ ያስዋብን አለን። ለመሆኑ በዚህ አመት ምን አዲስ መፅሐፍ ጀምረዋል? አንብበው ከጨረሱት መፅሐፍ ማንን ይመርጡልናል?    

 

"«አንብቡ አንብቡ አንብቡ፡ ኧረ እባካችሁ አንብቡ፤» ይህን ጽሑፍ ባነበብኩ ጊዜ የብዙ ፀሐፊያንን ልብ እንደ ሰበርን፣ የእውቀት እሳታቸውን ባለማንበብና በነቀፋ አፈር እንዳጠፋነው አሰብኩና ቆዘምኩኝ፡፡ ወደ ኋላ ዞር ብዬ በርተው የጠፉትን ከዋክብቶች ለአፍታ አሰብኳቸው፡፡ ቀጥሎም እንኳን ከባድ ሕይወትን ከባድ ቃላትን የማይመራመረውን የላይ የላይ ብቻ የሆነውን ዘመነኛ ሰው ታዘብኩ፡፡ እኔም ተመልካች ሳልሆን ተዋናይ ነኝና ራሴንም ወቀስኩ፡፡ «አንብቡ አንብቡ አንብቡ፤ ኧረ እባካችሁ አንብቡ፤»"
ደራሲ ዲያቆን አሽናፊ መኮንን


4 comments:

 1. የአገራችን ድህነት የሀብት ሳይሆን የአመለካከት መሆኑ ታውቋል፡፡ የዚህ ችግሩ ዋነኛው አለማንበብ ነው፡
  «አንብቡ አንብቡ አንብቡ፤ ኧረ እባካችሁ አንብቡ፤»

  ReplyDelete
 2. "ደራሲው ቃላቶችን ስብስቦ ስዕል ሲሆኑለት... በጋዜጣ፥ በመፅሔት ወይም በመፅሐፍ ያካፍለናል።
  ይህንን ስዕል ላለመመልከት አንገታችንን ያዞርን ብዙ ብንሆንም፤ ደራሲው ብዕሩን ሳያደርቅ የተዋቡ መፅሐፍቶችን አስረክቦናል።".... well done Bereket.
  መናገር ካለብኝ Cutting for Stone የሚባል መፅሐፍ በጣም ግሩም ነው surprisingly enough they're making the film so get the book and read it.

  ReplyDelete
 3. Maaza Mengiste's first novel, Beneath the Lion's Gaze I loved it and I would highly recommend it

  ReplyDelete
 4. እኔም ተመልካች ሳልሆን ተዋናይ ነኝና ራሴንም ወቀስኩ!!!!!

  ReplyDelete