28.2.14

ዝናቡ መጣ


ዘንድሮ የካሊኒፎርንያ ክረምት በደረቁ ሊያልፍ ነበር…
  


ፈጣሪ በቸርነቱ አስቦን ይኸው ላለፉት ቀናቶች ትንሽ ረጠብጠብ ብለናል። ሌላው ስቴት በዝናብም ሆነ በበረዶ ሲወጠር… የእኛው ፀሐይ አልጠልቅ ብላ ታሞቀን ነበር። 


ምንም እንኳን... አልፎ አልፎ ደመናማ ቢሆንም ዝናብ አልነበረንም።


የምንጠጣውን... የሚሞላ
የምንበላውን... የሚያለመልም
አምላክ አስቦናልና ተመስገን"ዝናቡ መጣ ዱብ ዱብ አለ
የዝናቡም ልጅ በሀይል ዘለለ"

እኛም… ልባችን በደሰታ ዘሏል፤ ነፋሳችንም በቸርነቱ ጠግቧልና አምላካችንን
 እናመስግን።

በረከት

26.2.14

ባርከን አመስግነን እንብላ

 በዚህ በአብይ ፆም ሳምንታቶች ብዙዎቻችን የተለያዪ ጥራጥሬዎች፥ አታክልትና ፋራፍሬዎችን እንመገባለን። 

የምንገዛባቸው የገበያ ቦታዎች ከየት እንደሚያመጡ፤ ምግቦቻችን እንዴት እንደሚመረቱ የምናውቅ በጣም ጥቂቶች ልንሆን እንችላለን።
በላቦራቶሪ ውስጥ የተፈጥሮ ዝርያውን የለወጠ
genetically modified organism (GMOs) or genetically engineered (GE) በላቦራቶሪ ውስጥ የተዳቀለ ወይም የተለወጠ... 


ወደ ቤታችን ይዘን ከመግባታችን በፊት፤ non-GMO በላቦራቶሪ ውስጥ ያልተዳቀለውን
የእህል ዘር ማለትም የተለያዪ አታክልት ፋራፍሬዎችና ጥራጥሬዎችን የሚያቀርቡትን ግሮስሪዎች እንፈልግ። 

ለመሆኑ በላቦራቶሪ ውስጥ የተፈጥሮ ዝርያውን የለወጠ ሲባል (GMOs) ምን ማለት ነው?
የተፈጥሮ መለያ ምንጭ የሆነውን DNA .ኤን. ውስጥ ሰው ሠራሽ በሆነ መንገድ... የአንድን የዘር ቅመም (genes) ነጥሎ በማውጣት፤ በሌላ ተዛማጅ ባልሆነ ዝርያ ውስጥ አስገድዶ በመጨመር የሚፈጠር አዲስ ዝርያ ማለት ነው  

ከእንደነዚህ አይነቶች ምግብ ራሳችንን እንዴት እንደምናድን የተለያዩትን ድህረ ገፆችን እንመልከት…

በአሁኑ ወቅት ገበያ ላይ ያሉት ዘጠኙ በላቦራቶሪ ውስጥ ዝርያቸውን የቀየሩ ምግቦች፤

The Nine genetically modified foods currently on the market are:


አልፋልፋ ጥራጥሬ ALFALFA  ካኖሊ  CANOLA 


 በቆሎ CORN cornstarch

ጥጥ እና የጥጥ ፍሬ ዘይት cotton and cottonseed oils 


ፓፓያ papaya (from Hawaii only)

ሶይ SOY soy lecithin

ስኳር ተጨምቆ የሚወጣበት Sugar made from sugar beets ( Sugar made from sugar cane is safe)

ZUCCHINI  ዝኩኒ 

YELLOW SUMMER SQUASH  ቢጫው ስኳሽ


ይበልጥ እንድናውቅ የሚረዱን የተለያዩትን ድህረ ገፆች፡ IMAGE CREDITS: google images


  ምግቦቻችን ሁሉ... ለስውነታችን፥ ለአካል ክፍሎቻችንና ለአእምሮቻችን የተስማሙ ይሆኑ ዘንድ ባርከን አመስግነን እንብላ ።

በረከት

24.2.14

ዘወረደ Zewered

The First Week of Lent 
   

ዘወረደ …የወረደ ማለት ሲሆን
ጌታ እኛን ለማዳንና ፍቅሩን ሊገልጽልን ከሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው።


Let us begin the Fast with joy and prepare ourselves for spiritual efforts…

When we fast lets other members of the body also need to fast: our eyes... from seeing evil, our ears... from hearing evil, our limbs... from participating in anything that is not of God.
And…our mouths…yes… lets control what comes out of our mouths. Are our words pleasing to God? Or…. our brother?

Most important of all, we need to control our thoughts, for thoughts are the source of our actions, whether good or evil.


እንኳን ለጌታችን ዐቢይ ጾም አደረሳችሁ

በረከት

20.2.14

የመፅሐፍ ባልንጀራ
ደራሲው ቃላቶችን ስብስቦ ስዕል ሲሆኑለት... በጋዜጣ፥ በመፅሔት ወይም በመፅሐፍ ያካፍለናል።
ይህንን ስዕል ላለመመልከት አንገታችንን ያዞርን ብዙ ብንሆንም፤ ደራሲው ብዕሩን ሳያደርቅ የተዋቡ መፅሐፍቶችን አስረክቦናል።

“አንድ መጽሐፍን ወደ ቤታችን ይዘን ስንገባ አንድ ባልንጀራ ይዘን ወደ ቤታችን መግባታችን ነው” ደራሲ ዲያቆን አሽናፊ እንዳሉት፥ ቤታችንን በብዙ ባልንጀራ ያስዋብን አለን። ለመሆኑ በዚህ አመት ምን አዲስ መፅሐፍ ጀምረዋል? አንብበው ከጨረሱት መፅሐፍ ማንን ይመርጡልናል?    

 

"«አንብቡ አንብቡ አንብቡ፡ ኧረ እባካችሁ አንብቡ፤» ይህን ጽሑፍ ባነበብኩ ጊዜ የብዙ ፀሐፊያንን ልብ እንደ ሰበርን፣ የእውቀት እሳታቸውን ባለማንበብና በነቀፋ አፈር እንዳጠፋነው አሰብኩና ቆዘምኩኝ፡፡ ወደ ኋላ ዞር ብዬ በርተው የጠፉትን ከዋክብቶች ለአፍታ አሰብኳቸው፡፡ ቀጥሎም እንኳን ከባድ ሕይወትን ከባድ ቃላትን የማይመራመረውን የላይ የላይ ብቻ የሆነውን ዘመነኛ ሰው ታዘብኩ፡፡ እኔም ተመልካች ሳልሆን ተዋናይ ነኝና ራሴንም ወቀስኩ፡፡ «አንብቡ አንብቡ አንብቡ፤ ኧረ እባካችሁ አንብቡ፤»"
ደራሲ ዲያቆን አሽናፊ መኮንን


14.2.14