20.1.14

ለጥምቀት ያልሆነ...


ለጥምቀት ያልሆነ ዝማሬ፤
ለሰኔ ያልሆነ በሬ

የጥምቀት ውበት፤ የጨረቃ ድምቀት... እንደተባለው ሁሉ ለጥምቀት ወይም
በጥምቀት ያልሆነ ሕይወት…ድምቀት ወይም ውበት የለውምና እናስተውል። 
ስባኪው “የክርስትና ዓላማው ግብረ ገብነት ሳይሆን ሕይወት ነው” እንዳሉት ሁሉ
ትህትናችን… ዝቅ ማለታችን ሁሉ ለግብረ ገብነት ብቻ ሳይሆን፥ እንደ ባለቤቱ ሕይወት፥ እንደ ባለቤቱ ብርሀን፥ እንደ ባለቤቱ ለመምሰል ነውና  

ከውኃና ከመንፈስ ተወልደን፥ የሥላሴን ልጅነት አግኝተን፥ እንደልጅ ካልኖርንና ካልሆንን በጥምቀት ያልሆነ ፍቅር በጥምቀት ያልሆነ አንድነት…. ወዴት ወዴት።


እንኳን ለጥምቀት በዓል አደረሳችሁ

በረከት

No comments:

Post a Comment