4.12.14

Picture of the Day የሚገርም ደመና

"ዳመናው ሲያንዣብብ በስማዩ ላይ
ዝናቡ ዝናቡ ልትመጣ ነው ወይ?..."
    
ዝናቡ  ለሁለት ቀናት ዘነበና ዛሬ የሚያስደንቅ ቀን ተወልን። እግዚአብሔር ይመስገን! ትንሽ ረጠብጠብ ብለናል።  ዝናቡ ሲዘንብ እኔም ቡቲ ጫማዬን አድርጌ.... እንደልጅነቴ "ዝናቡ መጣ ተንጠንባጠበ ብዬ" በሰተርጅናዬ ዘመን ተቀበልኩት። ዛሬ ደግሞ ይህንን የመስለውን ደመና ለመጥገብ በቅርብ ከሚገኘው ፓርክ ጎራ አልኩ። አይን ጠግቦ አይጠግብምና ፎቶ ማንሳቱን ተያያዝኩት።
የተዋበው ደመና  የሚገርምና የሚደንቅ ነፀብራቅ በውሀው ውስጥ ጥሎ ሄደ። 
በካሜራዬ የተነሳውን ፎቶ በኮምፒውተሬ ላይ ስመለከት ደነቀኝ።

Photo was taken… today at the Clark Regional Park in Buena Park, CA. 

27.11.14

Thanksgiving 2014


I praise You, O God of our Fathers, I hymn You, I bless You, I give thanks unto You for The great and tender mercy.

Thank You, O Lord, for our families and for everyone.... and everything.ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔር ባርኪ፥ ተቀኝለት ዘምሪለት፥ ሀጥያትሽን በደልሽ ሁሉ ይቅር ለሚል፥ በምህረቱና በቸርነቱ የሚጋርድሽን እግዚአብሔር ባርኪ።
ልዑል እግዚአብሔርን ሰለቤተስቤ ሰለሁላችሁም ሰለሁሉም አመስግነዋለሁ።

በልተን ጠጥተን ለምስጋና እንቁም ዘንድ አይነ ልቦናችንን ይግለጥልን።  ያዘነችውን የተከዘችውን ነፍስ ሁሉ ፈጣሪ ይጎብኛት። አሜን

በረከት

13.11.14

አየሮችን የሚያጠሩ የቤት ተክል

The Best Air-Purifying Plants


አዲስ ሆነ አሮጌ ቤት… መኖሪያ ቤቶቻችን በተለያዩ መጥፎ አየሮች ተበክለዋል።  ከተለያዮ ኬሚካል የተደበላለቀው ይህ የተበከለ አየር… የተጠረቃቀመው ከቀለም፥ ከፕታስቲክ፥ ከምንጣፍ፥ ከተለያዩ የቤት ማጽጃዎች(cleaning solutions) እና ህንጻውን ለመስራት ከተጠቀሙበት ቁሳቁሶች( numerous building materials) ነው።
   
ሶስቱ ዋነኛ የተበከሉት አየሮች formaldehydebenzene trichloroethylene  ሲሆኑ እነዚህን መጥፎ አየሮች ከመኖሪያ ሆነ ከመስሪያ ቤቶቻችን፤ የቤት ተክሎች በመትከል የምንተነፍስውን አየር ማጽዳት እንችላለን። አየሮችን ሊያጠሩ የሚችሉት አስሩ የቤት ተክሎች... 


English Ivy


Peace Lily


Bamboo palm (reed palm)


Red-Edged Dracaena

Dragon Tree


Heart Leaf Philodendron


Boston Fern

Golden Pothos
  
Snake Plant


Spider Plant

የተለያዩ መጥፎ አየሮችን እያጠሩ ቤታችንን ያሳምሩልናልና እንጠቀምባቸው።

በረከት

4.11.14

የቤት ተክል...አትክልት

Decorating with HouseplantsINTERIOR DESIGN IMAGE CREDITS: pinterest.com

የቤት ተክል ወይም አትክልት ቤታችንን ከማሳመር አልፎ፥ የተለያዩ መጥፎ አየሮችን ያጠሩልናልና እንጠቀምባቸው።

በረከት 28.10.14

የታለች ያቺ ወፍ?


"የታለች ያቺ ወፍ" የተባለውን ግጥም... ደራሲ አናኒያ መኮንን  ananyamekonnen.blogspot.com በሚባለው ድህረ ገጽ ካስቀመጠው ወራቶች አልፈዋል። እኔም እንደማንኛውም አንባቢ አንብቤ በአድናቆት የተሞሉትን ቃሎቼን ብወረውርም፥ የግጥሙ ቅኔ ልቤን ሰለነካው ለግጥሙ የሚሆን ስእሌን መሞነጭጨር ጀመርኩ። ወራቶችም አለፉ... በማስታወሻ ወረቀት የተሞነጫጨረው ስእል ቀን ወጣለትና ተሰሎ አለቀ። ደራሲ አናኒያ ሰለሰጠኝ ውበት ደግሜ እያመስገንኩ የደራሲውን ግጥምና የእኔን ስእል እነሆ።


የታለች ያቺ ወፍ
ደራሲ አናኒያ መኮንን

ያኔ ልጅ እያለሁ - ሰላም የምትለኝ
በሚያስደምም ዜማ - ልቤን የምትቃኘኝ
ቀኑ ደስ እንዲለኝ - ተስፋ የምትሰጠኝ
የታለች ያቺ ወፍ? - ዛሬ ስትናፍቀኝ
ከእንቅልፌ ስነቃ - ደስ በሚለው ዜማ
ኮለል ብሎ መጥቶ - በጆሮዬ ሲሰማ
የቀኑን ብሩህነት - ለነብሴ አብስራ
ታነቃቃኝ ነበር - መንፋሴን አድሳ
የታለች ያቺ ወፍ? - ዛሬ ስፋልጋት
ምነው አልዘፈነች - ነብሴ ሲናፍቃት
ምናል ብትመጣ - ልትሰጠኝ እርካታ
ዜማውን አፍልቃ - ብትሆነኝ እርጋታ
ግና ብትመጣስ - እንግባባ ይሆን
እንዲህ ተለያይተን - ብዙ አመቶች ከርመን
አንድ ያመሳሰለን - ጓደኞች ያረገን
የዋህነት ነበር - በፍቅር ያቀረበን
አሁን ታደገና - የዋህነት ቀርቷል
እንደ እባብ በተንኮል - መተያየት በዝቷል
መተዛዘን ቀርቶ - መጠቃቀም ሆኗል
ሀሳብ ልብም - ሲባክን ይውላል
አሁን ወፏ መጥታ - ጓደኞቿን ጠርታ
ስትዘፍን ብትወል - ኦርኬስትራ ሰርታ
ማን ሊያዳምጣት ነው - በበዛ ጫጫታ
ማንስ ይሰማታል - ታስረን በሁካታ


After reading, Ananya Mekonnen poem

የሚገርም ግጥም…. እንደእኔ ተስምቷችሃል? ጆሮ ያለው ይስማ ያስኛል። 
የደራሲው ብእር ትለምልም። 

በረከት

22.10.14

ተለወጥ Change


ስሞኑን ያንንም ይህንንም ስሰራ ስነበትኩ። የስእል እቃዎቼ በየስፍራው ተበታትነዋል፥ አንዳንዴ ብዙ የሚስሩና የሚፈጠሩ ነገሮች ይበዙብኝና አንዱን ጀምሬ ሳልጨርስ ወደሌላው እዛወራለሁ። የፈጣሪ ስሙ ይክበርና ይመስገን አእምሮዬም ከመፍጠር  እጆቼ ከመስራት አላቋረጡም፥ ድሮ ድሮ ይህ የፈጠራ ስራ ደረቅረቅ ሲል ውስጤ ሁሉ ደስ አይለኝም ነበር። መቼም ስው...  የእግዚአብሔር ስው ሆኖ... ለበጎ የማይቀየር.... በበጎ የማያድግ ከሆነ ውስጡን በሚገባ መመርመር አለበትና። ታዲያ.... እኔም እያደርና እየዋለ የፈጠራ ሳራ መጣ አልመጣ.... ደረቀ አልደረቀ.... ብዬ ራሴን አላስጨናንቀውም። ስእሎቼን ከሳያልኩ በደስታና በጸሎት.... የሚሳልም ከሌለ በደስታና በጸሎት መቀበሉን ተማርኩ።
አንዳንዴ ሳናውቀው ተለውጠን እንገኛለን፥ መለወጣችን ሁሉ ለመልካምነት ከሆነ ብዙ ፍሬ እናፈራለን። ትግስቱን ትህትናውን አስተዋይነቱን....   እነዚህን ሁሉ እናፈራለን። ግን.... ግን መለወጣችን ለዓለም እና በዓለም ከሆነ  ፍሬ እንደማያፈራ ዛፍ ሆነናል። 
የአባታችንን የአብርሃምን ታሪክ ሳስበው በጣም ይገርመኛል። ከተወለደበት ከተከበረበት ሀገር ወጥቶ የት እንደሚሄድ ሳያውቅ በእግዚአብሔር ስለተጠራ ለመለወጥ አቤት ማለቱ ያስደንቀኛል። 
ለመለወጥ አቤት ማለት
ለመለወጥ ከጓዳ መውጣት
ለመለወጥ ዝግጁ መሆን 
እንዴት መባረክ ነው?
በተለይ በዚህ ዘመን መለወጣችን እንዴት ነው? መለወጣችን ለማን ነው? ስንለወጥስ ስንቶችንን አስደስተናል ወይስ አሳዝነናል? “Growth means change and change involves risk, stepping from the known to the unknown.” 

"By faith Abraham obeyed when he was called to go out to a place that he was to receive as an inheritance. And he went out, not knowing where he was going."  Hebrews 11:8

"አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ።"  ወደ ዕብራውያን 11:8

በረከት