3.12.13

የክረምት ፀሐይ....ስትጠልቅ

"ደመናን ሰንጥቃ - ጤዛውን ልታተን - ብቅ እንዳለች ጮራ
ባልጠግብ ባይነት - እንደምንሞቃት - ከአቻዎቼ ጋራ
ሙቀቷን ሳናውቀው - ግለቷም ሳያመን
በልስልስ ጨረሯ ...
ሀሴት ለውስጣችን
ሙቀት ለገላችን - እንደምትመግበን፤
ካፊያን እንድንረግም - ጉም እንድንጠላ - እንደምታደርገን
‹‹ምናለ በወጣች!›› - እንደምታስበለን - እንደምታጓጓን..." 
ግጥም በደመቀ ከበደ
"ፍቅር ይዞኝ ነበር"  ላይ የተወስደ

Photo was taken in Ted Craig Regional Park, 3300 State College Blvd Fullerton, CA 92832

አዎን የክረምት ፀሐይ....ስትጠልቅ... በደመና ተውባና ታጅባ ነው። ገጣሚው እንዳለው "ሙቀቷን ሳናውቀው - ግለቷም ሳያመን" ውበቷን አእምሮአችን ውስጥ ከትባ ትጠቀለላለች። አዎን የክረምት ፀሐይ በደመና ተውባና ታጅባ ትወጣለች... በደመና ተውባና ታጅባ ትጠልቃለች። እናስተውል!

በረከት

No comments:

Post a Comment