21.11.13

ተነሥ፥ ተነሥ ... Awake, awake2045 Sawtelle Blvd በራቸውንና መስኮቶቻቸውን ቢዘጉብንም እኛ ጥቁር ለብስን፥ የተስበረ ልብ ይዘን፥ በመንገዱ ግራና ቀኝ ላይ ተስበስብን።
የስሚ ያለ... የታዛቢ ያለ... ብለን ኡኡ አልን፥ እስትንፋስ ያለው ሁሉ ለወገኑ ጮኸ። ጩኸታችን ወደ ፀሎት እንዲለወጥ ቄሶቻችን ሁሉ መጡ። መስብስባችንንም ባረኩ።

እኛው ተጯጯኸን እንጂ ስሚም ታዛቢም አልነበረንም። ሚዲያ ሁሉ የት ገባ? ትልቁንም ትንሹንም ወሬ ፈላጊ ጋዜጠኛ ሁሉ ዛሬ የታለ?

ስሚም ታዛቢም ፈራጅ አምላካችን እሱ ይቁምልን። የእርሱ ክንድ ይነሳ። እንባችንን እርሱ ያብስ እንጂ… እኛማ ማን አለን?

የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ ተነስ ለኛ
ከጥንት የነበረው ታላቅ ግሩም ኃይል
 ዛሬም ይንቀሳቀስ ለኛ”

አዎን ያ ድንቅ ኃይል..  ግሩም ኃያል ኃይል  ለኛ ይንቀሳቀስልን እንጂ… እኛማ ማን አለን?    ኢሳይያስ 51: 9   
የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ፥ ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ፤ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?

Isaiah 51: 9
Was it not you who pierced that monsterthrough?
 ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?
አንተ አይደለህምን???

በረከትNo comments:

Post a Comment