16.11.13

መከር ገባና.. Autumn..
መከር ገባና ቅጠሎች ተቀያየሩ። ፀሀይ ባትወጣም፥ በውበታቸው አካባቢያቸውን አሞቁት።

መከር ገባና...
 ሰዓታቸውና ወቅታቸውን ጠብቀው ቅጠሎችም ረገፉ።

   ያለወቅቱ....ግዜው ሳይደርስ ለሚረግፈው...
ያለእድሜው ለሚቀጨው ለዘመኑ ሰው አዘንኩ። የመከር ቅጠል እንኻን በልጦት።
በአንድ እጅብ ብለን ሳለ፥ ፀሀይ ባትወጣም፥ በውበታችን አካባቢያችንን አሙቀንንና አድምቀን ሳለ፥ ድንገት ሳናስበው እናታችን አንገቷን ደፋች። እኛም ተበታተንን።
ተበታትነንም አንቀርም እንስባስባለን... እናታችንም አንገቷን ታቀናለች... ያ ቀን ይመጣልና ተስፋ አንቁረጥ... እስከዚያው ድረስ ግን እጃችንን እናንሳ...  በሳዑዲ አረብያ የመከራ ማጥ ውስጥ ላሉት ወገኖቻችን እግዚኦ እንበል።
        
   


የአባቶቻችን አምላክ ለልባችሁ ፍቅር፥ ለነፍሳችሁ ስላም፥ ለህይወታችሁ ደስታ ይስጣችሁ።

በረከት

1 comment:

  1. Berry...Have I told you lately how much I LOVE your photography!! ;)

    ReplyDelete