29.11.13

ጥቁር አርብ...Black Friday


ትናንት የምስጋና ቀናችንን (Thanksgiving Day) እንደሀገሩ ደንብ ተስባስበን በምስጋና አከበርን። 
ዛሬ... ጥቁር አርብ Black Friday  (the day after Thanksgiving)  ታላቅ ቅናሽ የገበያ ቀን ስለሆነ ብዙዎች ወደገበያ ሲሄዱ፥ አንዳንዶች ወደስራ… አንዳንዶቻችን ደግሞ ለበአሉ ከመጡት እንግዶች ጋር ጨዋታችንን እናደራለን።  እኔም ከነዚህ ውስጥ አንዱ ነበርኩና ጥቁሩን አርብ በሀገራችን ባህል አሽሞነሞንኩት።    


በረከት

26.11.13

የምስጋና ቀን...Thanksgiving place card ideas
ልዑል እግዚአብሔር የምስጋና ቀናችንን ይባርክልን። በልተን ጠጥተን ለምስጋና እንቁም ዘንድ አይነ ልቦናችንን ይግለጥልን።  ያዘነችውን የተከዘችውን ነፍስ ሁሉ ፈጣሪ ይጎብኛት። አሜን

May your Thanksgiving be filled with God's blessings and Joy for you and your family. 

Bereket

21.11.13

ተነሥ፥ ተነሥ ... Awake, awake2045 Sawtelle Blvd በራቸውንና መስኮቶቻቸውን ቢዘጉብንም እኛ ጥቁር ለብስን፥ የተስበረ ልብ ይዘን፥ በመንገዱ ግራና ቀኝ ላይ ተስበስብን።
የስሚ ያለ... የታዛቢ ያለ... ብለን ኡኡ አልን፥ እስትንፋስ ያለው ሁሉ ለወገኑ ጮኸ። ጩኸታችን ወደ ፀሎት እንዲለወጥ ቄሶቻችን ሁሉ መጡ። መስብስባችንንም ባረኩ።

እኛው ተጯጯኸን እንጂ ስሚም ታዛቢም አልነበረንም። ሚዲያ ሁሉ የት ገባ? ትልቁንም ትንሹንም ወሬ ፈላጊ ጋዜጠኛ ሁሉ ዛሬ የታለ?

ስሚም ታዛቢም ፈራጅ አምላካችን እሱ ይቁምልን። የእርሱ ክንድ ይነሳ። እንባችንን እርሱ ያብስ እንጂ… እኛማ ማን አለን?

የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ ተነስ ለኛ
ከጥንት የነበረው ታላቅ ግሩም ኃይል
 ዛሬም ይንቀሳቀስ ለኛ”

አዎን ያ ድንቅ ኃይል..  ግሩም ኃያል ኃይል  ለኛ ይንቀሳቀስልን እንጂ… እኛማ ማን አለን?    ኢሳይያስ 51: 9   
የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ፥ ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ፤ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?

Isaiah 51: 9
Was it not you who pierced that monsterthrough?
 ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?
አንተ አይደለህምን???

በረከት19.11.13

Stretch out your hand... እጅህን አንሳ


Imagine this: You are poor. You need food, water, shelter, medicine,  basics of life, so much more for those you love than yourself, for children, for your helpless family. So you seek this where you can. You go where you are alone and work hard and long. Then, where you are, where you have worked for so long, authorities decide you are no longer wanted, so they beat you and rape you and imprison you. You turn and find you have no place to go.

Riyadh’s Ethiopian immigrants have been subjected to murder, rape and beatings in savage Saudi outrages against them. To the Saudi regime, their crime is that they are Ethiopian. Saudi officials say, “These people were born to be destitute.”

We cannot stand by silently and allow them to continue in their persecution of defenseless Ethiopians. Can we do anything? Can we share the shame and destitution of our family across the miles? If you ­believe that families are stronger when they are united, let’s be a family to our sisters and brothers. Lets give some of our time by standing and giving voice in front of the Saudi Embassy together, to say that self-righteous cruel bigots of all the countries involved should be held accountable for their crimes committed against humanity.

And let’s see where our elected representatives stand. Let’s see if we hear a call to action or platitudes.

Most of all, let us not forget our family of all people. LET US BEGIN.
Meet us there.
TomorrowNovember 20, 2013 at 12pm 
 Saudi Arabia Embassy 
2045 Sawtelle Blvd
Los Angeles, CA, 90025


ለወገንህ ለእህትህ ለወንድምህ እጅህን አንሳ... እጅሽን አንሺ
ጉልበትህ ሰዓትህ ነው
  ገንዘብህ አቅምህ ነው
ድምፅህ... ፀሎት ማንነትህ  ነውና
እጅህን አንሳ

ሰዓትህ አድርግ
በአቅምህ እርዳ
ፀሎት በህብረት ቁም።

ማቴ 25:35-40
"ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥... 
ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።... እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ለወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሗልና  ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ" 

ወገንህ ተርቧል ወገንህ ተጠምቷል ወገንህ ታስራልና ጠይቅ
 መቼ ? የት?  ላልከው ሁሉ ግዜው አሁን ነውና ተንስ  እጅህን አንሳ ትጠየቅበታለህለወገኔ ለእምዬ ልጆች፥ እግዚአብሄር የሚያፅናናውን መንፈስ ቅዱስ ያውርድላቸው። ተስፋቸውን ያለምልም። እንባቸውን ይዳብስ። ስብራታቸውን ይጠግን። የወገን ያለ ብሎ ለጮኸ ሁሉ ወገኑ ይድረስው።

በረከት
  

16.11.13

መከር ገባና.. Autumn..
መከር ገባና ቅጠሎች ተቀያየሩ። ፀሀይ ባትወጣም፥ በውበታቸው አካባቢያቸውን አሞቁት።

መከር ገባና...
 ሰዓታቸውና ወቅታቸውን ጠብቀው ቅጠሎችም ረገፉ።

   ያለወቅቱ....ግዜው ሳይደርስ ለሚረግፈው...
ያለእድሜው ለሚቀጨው ለዘመኑ ሰው አዘንኩ። የመከር ቅጠል እንኻን በልጦት።
በአንድ እጅብ ብለን ሳለ፥ ፀሀይ ባትወጣም፥ በውበታችን አካባቢያችንን አሙቀንንና አድምቀን ሳለ፥ ድንገት ሳናስበው እናታችን አንገቷን ደፋች። እኛም ተበታተንን።
ተበታትነንም አንቀርም እንስባስባለን... እናታችንም አንገቷን ታቀናለች... ያ ቀን ይመጣልና ተስፋ አንቁረጥ... እስከዚያው ድረስ ግን እጃችንን እናንሳ...  በሳዑዲ አረብያ የመከራ ማጥ ውስጥ ላሉት ወገኖቻችን እግዚኦ እንበል።
        
   


የአባቶቻችን አምላክ ለልባችሁ ፍቅር፥ ለነፍሳችሁ ስላም፥ ለህይወታችሁ ደስታ ይስጣችሁ።

በረከት

12.11.13

ለስዕል አፍቃሪዎች... "ዘፍጥረት"

 ያለፉት ሳምንታት ውስጥ... ይህንን ስዕል ስዬ አስረከብኩ። 
 ለባለቤቱ... ቢሆን... እህህህ  
ወልዶ አሳድጎ.... ለባለቤቱ
አበልቶ አጠጥቶ አልብሶና አስተምሮ.... ለባለቤቱ
ለነገሩ እኮ ባለቤቱም ሲስጥ አሳምሮና ዋጋ ከፍሎበት ነበር፥ እኛ አልገባ አለን እንጂ 
በረከት