30.10.13

የዱባ ወጥ


የጥቅምት ወር ማለቂያው ላይ ከሚከበረውን ሀሊውን Halloween ጋር ትብብርና ህብረት ባይኞረኝም እንኻን... በዚህ ወቅት የዱባ አትክልት ዋጋው ቀነስነስ ስለሚል... የዱባ ወጥና የዱባ ዳቦ ለመስራት እኔም እንደሌሎቹ ሁሉ የዱባን አትክልቴን ይዤ ወደቤቴ እገባለሁ። 


የዱባ ወጥ
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች

¼ ስኒ የወይራ ዘይት (olive oil)
2 ቀይ ሽንኩርት፥የደቀቀ
2  የሾርባ ማንኪያ በርበሬ
3 ነጭ ሽንኩርት ድቅቅ ያለ  
5  ስኒ የተከታተፈ ዱባ (about 3 pounds)
1 የሻይ ማንኪያ ነጭ ቅመም
የሻይ ማንኪያ መከለሻ 
2  የሻይ ማንኪያ ጨው
1 እግር (ዝንጣፌ) እርጥብ በሶብላ 

አዘገጃጀት
በወጥ ድስት ውስጥ የወይራ ዘይቱ ሞቅ ማድረግ፥ከዚያ የደቀቀውን ቀይ ሽንኩርት መጨመርና ማቁላላት፥ ሽንኩርቱ ቡናማ ሲመስል በርበሬውን መጨመር፥ እንዳያር ትንሽ ውሀ ጠብ እያደረጉ ማሽት፥ ወደ 20 ደቂቃ ይፈጃልና እንዳያር መጠንቀቅ።
ነጭ ሽንኩርት፥ የተከታተፈውን ዱባና ግማሽ ስኒ ውሀ ይጨምሩና ያዋህዱት። ከ15 ደቂቃ በሓላ፥ ወይም ዱባው በስል ሲል… ሳይሞክክ በፊት... ነጭ ቅመም፥መከለሻና ጨው  መጨመርና ማውጣት።
በሶብላውን ጣል ማድረግ።

ቀዝቀዝ ሲል (Let cool to room temperature) ለገበታ ማቅረብ

Ethiopian Pumpkin Duba wet recipes in english

የዱባ ፍሬ ለጤና ብዙ ጥቅም አለውና በደንብ ካጠቡት በሃላ ይቁሉት።


Nutrients in Pumpkin Seeds 
manganese  tryptophan magnesium phosphorus copper protein zinc Iron 

  

 

 በሚቀጥለው ደግሞ የሚጣፍጠውን  የዱባ ዳቦ አብረን እንጋግራለን።
እስከዚያው ድረስ ... በሞቴ!.... አፈር ስሆን ልበላችሁ

 

    ምግቦቻችሁ ሁሉ... ለስውነታችሁ፥ ለአካል ክፍሎቻችሁና ለአእምሮቻችሁ የተስማሙ ይሆን ዘንድ ባርካችሁ ብሉ ።

በረከት

1 comment:

  1. ምግቦቻችሁ ሁሉ... ለስውነታችሁ፥ ለአካል ክፍሎቻችሁና ለአእምሮቻችሁ የተስማሙ ይሆን ዘንድ ባርካችሁ ብሉ ።

    ReplyDelete