16.10.13

የራሺያ የእንጨት አሻንጉሊት


በአንድ ወቅት አትዮጵያ ውስጥ የራሺያ የእንጨት አሻንጉሊት ሽሚኒያቸው (fireplace mantels) ላይ ያላስቀመጡ አልነበሩም። ታዲያ ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ የግማሾቻችን ጠፋብን ወይም ተስበረብን። የአንዳንዳችን ደግሞ አስካሁን ተከብሮ ተቀምጦል። የኔዋ እናት እቃ በማስቀመጥ፥ አስቀምጦም ለሚቀጥለው ትውልድ ማስረከብ ከእናቷ የወረስችው አንዱ ታላቅ ሙያዋው ነውና ተጠቅልሎ ወደእኔ ቤት ገባ። በእናቴ ቤት ሲቀመጥ ወደ ስላሳ አመት የሞላውን ይህን የእንጨት ስራ ስረከብ፥ ልጅነት ትዝታዬ እጅ ነስቼ ነበር።
በእጄ ከገቡም በሓላ፥ ስለነሱ ለማወቅ ብዙ ግዜም አልወስደብኝም።

Matryoshka doll ወይም Russian nesting ሲባል በእኛው አገር አባባል የምትወልደዋ አሻንጉሊት ትባላለች።
የመጀመርያው የራሺያ የእንጨት አሻንጉሊት የተስራው በ1890 ላይ በ  Vasily Zvyozdochkin ነበር...

ታዲያ እርሶም... በእጅ ተፈልፎሎበእጅ የተቀባው፥ የድሮው የራሺያ የእንጨት አሻንጉሊት ካሎዎት ዋጋው ከስልሳ እስከ ስማኒያ ዶላር ወይም ከዚያም በላይ ይገመትሎታል።
Wooden Rooster and Chicks Russian Nesting Dolls. 
የአውራ ዶሮ፥ የዶሮና የጫጩት አሻንጉሊት

በረከት 


No comments:

Post a Comment