30.10.13

የዱባ ወጥ


የጥቅምት ወር ማለቂያው ላይ ከሚከበረውን ሀሊውን Halloween ጋር ትብብርና ህብረት ባይኞረኝም እንኻን... በዚህ ወቅት የዱባ አትክልት ዋጋው ቀነስነስ ስለሚል... የዱባ ወጥና የዱባ ዳቦ ለመስራት እኔም እንደሌሎቹ ሁሉ የዱባን አትክልቴን ይዤ ወደቤቴ እገባለሁ። 


የዱባ ወጥ
አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች

¼ ስኒ የወይራ ዘይት (olive oil)
2 ቀይ ሽንኩርት፥የደቀቀ
2  የሾርባ ማንኪያ በርበሬ
3 ነጭ ሽንኩርት ድቅቅ ያለ  
5  ስኒ የተከታተፈ ዱባ (about 3 pounds)
1 የሻይ ማንኪያ ነጭ ቅመም
የሻይ ማንኪያ መከለሻ 
2  የሻይ ማንኪያ ጨው
1 እግር (ዝንጣፌ) እርጥብ በሶብላ 

አዘገጃጀት
በወጥ ድስት ውስጥ የወይራ ዘይቱ ሞቅ ማድረግ፥ከዚያ የደቀቀውን ቀይ ሽንኩርት መጨመርና ማቁላላት፥ ሽንኩርቱ ቡናማ ሲመስል በርበሬውን መጨመር፥ እንዳያር ትንሽ ውሀ ጠብ እያደረጉ ማሽት፥ ወደ 20 ደቂቃ ይፈጃልና እንዳያር መጠንቀቅ።
ነጭ ሽንኩርት፥ የተከታተፈውን ዱባና ግማሽ ስኒ ውሀ ይጨምሩና ያዋህዱት። ከ15 ደቂቃ በሓላ፥ ወይም ዱባው በስል ሲል… ሳይሞክክ በፊት... ነጭ ቅመም፥መከለሻና ጨው  መጨመርና ማውጣት።
በሶብላውን ጣል ማድረግ።

ቀዝቀዝ ሲል (Let cool to room temperature) ለገበታ ማቅረብ

Ethiopian Pumpkin Duba wet recipes in english

የዱባ ፍሬ ለጤና ብዙ ጥቅም አለውና በደንብ ካጠቡት በሃላ ይቁሉት።


Nutrients in Pumpkin Seeds 
manganese  tryptophan magnesium phosphorus copper protein zinc Iron 

  

 

 በሚቀጥለው ደግሞ የሚጣፍጠውን  የዱባ ዳቦ አብረን እንጋግራለን።
እስከዚያው ድረስ ... በሞቴ!.... አፈር ስሆን ልበላችሁ

 

    ምግቦቻችሁ ሁሉ... ለስውነታችሁ፥ ለአካል ክፍሎቻችሁና ለአእምሮቻችሁ የተስማሙ ይሆን ዘንድ ባርካችሁ ብሉ ።

በረከት

24.10.13

የማያረጅ የዳንቴል ቁንጅና... ክፍል ሁለት


እንደዛሬው የቲቪ ጣቢያዎች ሳይበዙ፥ የእጅ ስልክ እንደንቅሳት በእጃችን ሳይታተሙ፥ ኮምፒውተር ላይ አይናችን ሳይፈጥ… ትናንት ዱሮ ሳይሆን… እናቶቻችን እና ኮረዳዎቻቸው ክሩን በኪሮሽ ጠላልፈው ዳንቴል ይሰሩ ነበር።
የቲቪ ልብስ፥ የሶፋ ልብስ (Sofa back doily)፥ የጠረጴዛ ልብስ (Coffee Table Doily)፥ የአልጋው ልብስ (Crochet Bedspread)… አረ ምኑቅጡ የአንገት ልብስና ባርሜጣውን ሁሉ በባለሙያዎቻችን ይስሩ ነበር።
እኔም እንደብዙሀኑ ጭቃውን ከአድበለበልኩ፥ ሀሁንና አቦጊዳን ከፃፍኩ በሓላ… እጆቼ የተፍታቱት በዳንቴል ስራ ነበር። አንድዮሽ፥ ሁለትዮሽ ሶስትዮሽ... 
አልጋ ልብስን ያህል ባይዋጣልኝም እንኻን፥
 የሶፋ የቲቪና የጠረጴዛ ልብስ (living room doily set) አሳምሬ ስርቼው ነበር። ትናንት ዱሮ ሳይሆን…
INTERIOR DESIGN IMAGE CREDITS: pinterest.com and google images 


ዘፍጥረት 37፥
ተባረኩ፥ የብዙ ሕብረ ቀለማትን ያለበትን ካባ ያልብሳችሁ።

May God bless you all abundantly and may you to wear the coat of many colors.

The coat of many colors symbolizes all the gifts and fruits of the Spirit blessings..... all the favor of God, His divine grace, power and love.

Bereket

21.10.13

የማያረጅ የዳንቴል ቁንጅና... ክፍል አንድ


እሷ...
የዳንቴል ሹራብ ፋሽኑ ነው አሉ
ለደረተ ስፊ ለሚገኝ በቃሉ
የልብህ አድርገኝ የኔ አመለ ውብ
እስራልሀለሁ የዳንቴል ሹራብ

እሱ...
የኔ ባለሙያ አመለወርቅ ነሽ
ከልቤ ገብተሻል አምሮብሽ ተቀምጠሽ
አረንጋዴ ቢጫ ኮሌታው ያማረ
ስሪልኝ ሹራቡን የተዥጎረጎረ

chairs49


chair56By Aterlier Abigail Ahern via Livingetc


INTERIOR DESIGN IMAGE CREDITS: pinterest.com and google images 


ክፍል ሁለት... የተለያዩ ቀለማት ያላቸው ዳንቴሎች ቁንጅናቸውን እናያለን።  
 በስላም ቆዪልኝ። 
የብዙ ሕብረ ቀለማትን ያለበትን ካባ ያልብሳችሁ።


በረከት