26.9.13

በትንሿ ኢትዮጵያ ስፈር

አሮጌው ዓመት አልፎ አዲሱ ዓመት መጣ፥ ሁላችንም… ተቀበልነው።
ዘመነ ማርቆስም ተባለ።
ፍቅርን ለሚያጠብቃት ሆነ ለሚያላላት፥ ስላምን ለሚገነባት ሆነ ለሚያፈርሳት፥ ተስፋን ለሚናፍቃትና እምነት ለሚጨብጣት ሁሉ… ለጻዲቁም ሆነ ለኅጢያተኛው፥ ለሁሉም አዲስ ዓመት ተሰጠው።

እዚህ ያለነው እንቁጣጣሽን ለማክበር በትንሿ ኢትዮጵያ ስፈር ተስብስበን ነበር።
የተመቸው ሁሉ መጣ።


እኔም ትንሿን ካሜራዬን ይዤ አንዣብቤ ነበር። ካሜራዬም እኔንም ጨምራ ብዙ አነሳች።
ከዛ ሁሉ ትርኢትና ዝግጅት፥ ከነበረው ስው ቁንጅናና አለባበስ፥ ካሜራዬና እኔ ከሶስት ህፃናት ልጆች ጀርባ ቆምን። አስተዋልኩም… በአየሁት እይታ ረካሁ፥ ቀጭ ቀጭ አድርጌ ቀረፅኳቸው።
ከትንሿ ኢትዮጵያ ስፈር 
የተስጠኝን መልእክት ይዤ ወደቤቴ ገባሁ።
 በቀለሜ ቀለምኳቸው… ሳልኳቸው።


ተስፋ እምነትና ፍቅር ብዬ ስየምኳቸው።


አዎን አዲስ ዓመት ሁልግዜ የተስፋ የእምነና የፍቅር መጀመርያ ናቸው። ሁሉም ይመኛቸዋል... ይመርቃቸዋልም። አዲሱ ዓመት ካለፈስ በሗላ… ተስፋ እምነና ፍቅር ይከተሉን ይሆን?  


እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው  ፍቅር.. ትንሽም ቢሆን እንኻን ያለውን ለመስጠት አይቆጠብም ..ይንጠራራልናበረከት 

11.9.13

2006


እዮሀ አበባዬ መስከረም ጠባዬ...
እንኻን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ።


መዝሙረ ዳዊት 90፤11
በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ሰለ አንተ ያዝዛቸዋል ይላልና
በዚህ ዓመት እግሮችዎና እጆችዎ እንዳይስናከሉ አንደበቶትና ልቦናዎ እንዳይጎድፉ፥ ውስጣዊው ባሕርይዎት ሁሉ በአምላክ ፊት ያማረ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መላእክቶች ከአጠገብዎ ይቁሙሎት፥ እጃቸውን ያንሱሎዎት  መንገድዎንም ያስተካክሉሎት።
መልካም አዲስ አመት!


I pray that the grace of God will carry you through each new year and that with each new challenge or trouble that may come your way, God will give His mighty, powerful, warrior angels charge over you lest you dash your foot against a stone. I pray that you will not fear, and you will not harm  as you fight the good fight to its glorious end.
Psalm 91:11


Happy Ethiopian New Year 2006 !
በረከት