29.8.13

ሙልሙል ዳቦ... ክፍል ሁለት

ሙልሙል ዳቦ በወይራ ፍሬ ድልህ


አዎን  የልጅነት ትዝታ እሩቅ አይደለችም… ሙልሙል ዳቦም ባህር ተሻግራ ትመጣለች   የኮባው ቅጠሉ የኩበቱ ጭሰ ቃና ሁሉ ይዛ ለሙልሙል ምንም ማባያ ባያስፈልገውም እንዃን
በአበሻ ዳቦ ሆነ በፈረንጅ ዳቦ ላይ ለቅለቅ አድርገው የሚያባሎት  በጣም የሚያረካ የወይራ ፍሬ ድልህ አዘገጃጀት እነሆ


 የወይራ ፍሬ ድልህ (Tapenade)

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች: 

2 ስኒ (የምግብ መለኪያ ስኒ) ፍሬው የወጣለት የወይራ ፍሬ የተደበላለቀ ወይም ካላሜታ
3 አንቾቪ anchovy fillets (በጠርሙስ የታሽገ በጣም ትንንሽ ዓሳዎች)
2 የሾርባ ማንኪያ ኬፐር capers (በጠርሙስ የታሽገ በጣም ትንንሽ ፍሬዎች)
አንቾቪና ኬፐር ማግኘት አስቸጋሪ ከሆነ ነጭ ሽንኩርትን ጨመር ያድርጉ 
2 ነጭ ሽንኩርት
የአንድ ሎሚ ጭማቂ
ግማሽ የሾርባ ማንኪያ የተከተፈ የፈረንጅ በሶብላ basil (የፈረንጅ በሶብላ ከአበሻው በሶብላ ጣፈጥ ይላል)
ግማሽ የሾርባ ማንኪያ የተከተፈ ጠፍጣፋው የሾርባ ቅጠል flat-leaf parsley leaves
ግማሽ  የሾርባ ማንኪያ የተከተፈ ጦስኝ thyme leaves
¼ ስኒ የወይራ ዘይት
ትንሽ ብትን ቁንዶ በርበሬና የደረቀ የቃርያ ፍሬ

አዘገጃጀት

  የወይራ ፍሬውን በደንብ በቀዝቃዛ ውሀ ለቅለቅ ማድረግ። ከወይራ ዘይት በስተቀር በምግብ መፍጫ ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን በሙሉ ማደባለቅና ቀስ እያሉ መፍጨት። ከተፍተፍ ያለ ድልህ እስኪመስል እያደባለቁ መፍጭት። በወይራ ዘይቱ ለውሶ ከጠርሙስ በተሰራ እቃ ገልብጦ ማቀዝቀዣ ውስጥ ማስቀመጥ። 
በህይወቶት ቀምሰው የማያውቁት... የበረከት የወይራ ፍሬ ድልህ
 እምም…Hemmmm ያስኛል።  

 Tapenade (yeweyra fre deleh)


Ingredients:

2 cups pitted Kalamata olives or mixed olives
3 anchovy fillets, rinsed
2 tablespoons capers
2 cloves of garlic
Juice of one lemon
1/2 tablespoon chopped fresh basil leaves
1/2 tablespoon chopped fresh flat-leaf parsley leaves
    1/2 tablespoon chopped fresh thyme leaves
1/4 cup extra-virgin olive oil
Freshly ground black pepper

Directions:

Thoroughly rinse the olives in cool water. In a food processor combine all the ingredients except the olive oil. Process to combine, stopping to scrape down the sides of the bowl, until the mixture becomes a coarse paste, approximately 1 to 2 minutes total. Continue to process, slowly adding the olive oil. Refrigerate in a covered container. Use as needed. yamme yamme

May all your meals be joyous and scrumptious.


ሙልሙል ዳቦ
ሙልሙሌ በምንም ትበያለሽ.... 
   
በረከት

23.8.13

የልጅነት ትዝታ… ሙልሙል ዳቦ

ክፍል አንድበቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መስረት ከሰባቱ ዓበይት አጽዋማት አንዱ ጾመ ፍልሰታ (Assumption of Mary) ትናንት ተፈስገ። እኛም ደመቅ አድርገን አከበርንና ይህንንም ያንንም ለመመገብ ተስበስብን። የኔው ሆድ ያስበውን ያውቃልና ትንሽ ቀመስ ቀመስ አድርጎ ሆያሆዬ ሳይል የስበስበውን ሙልሙል ዳቦ ለመብላት ተነሳሳ።

 

"እርግብ ስትቀመጥ
ዳቦህን ግመጥ
እርግብ ስትነሳ
ዳቦህን አንሳ"
 እንደ ተባለው ሙልሙል ዳቦዬን አነሳሁ... በሆዴም…  


"ሆያ ሆዬ  ሆ  ሆያ ሆዬ ሆ
እዛማዶ ጭስ ይጨሳል
አጋፋሪ ይደግሳል
ያንን ድግስ ውጬ ውጬ
በድንክ አልጋ ተገልብጬ
ያችም ድንክ አልጋ አመለኛ
ያለ አንድ ሰው አታስተኛ"


አልኩና ሙልሙሌን እንደ ልጅነት ትዝታዬ በሻይ እያጠቀስኩ በላሁ።


 Hemmmm…
 የልጅነት ትዝታ ለካስ ይበላል… ይገመጣል…  የኮባው ቅጠል፥ የጭሱ ቃና ሁሉ ሲጣፍጥ  yam yam delicious.It was so, so good... like... bread pudding!
እንኳን አደረሳችሁ።

በረከት

15.8.13

ይቻላል ይቻለኛል ይሆናልሰዓሊው በመጀመሪያ በአእምሮ አይኑ ያየውንና ያስበውን በልቦናው ያወጣውንና ያወረደውን፥ በወረቀት ላይ ሞኖጫጭሮ ጨምቆ እስኪያወጣው ድረስ እረፍት የለውም።


ከውስጡ ሳያፈልቀው በፊት... በአይነ ልቦናው የፍጥረቱን ውበት ይመለከታል። ደስታና እርካታ ከስጠው ይቻላል ብሎ ያስባል። አስቦም አያስቀረውም።


 ይቻላል ያለውን ስነጥበብ ይቻለኛል ብሎ ያወጣዋል፥ ሲያወጣውም ይሆናል ብሎ አይጀምርም። አንዳንድ ግዜ አይሆንምና። ሰለዚህም በአእምሮ የሳለውን በወረቀቱ ላይ ቀልሞ ቀላልሞ እስከሚሆን ድረስ ይሞክራል። ያኔ በአእምሮ አይን ያየውና ፤ወረቀቱ ላይ የተሳለው፤ሲመሳስሉ ሆነ ያላል። 


ታድያ እኔም ይህንን የወፍ ወጥመድ ስመለከተው፥ ከዚያም ከዚህ የተጠረቃቀሙትን ስእሎች በግርጊዳው ላይ ሳለጥፍ በፊት በስዓሊው ልቦናዬ ሁሉንም ቀድሜ አየሁት። ይቻላል … ይሆናል አልኩ።...ሁላችንም ፈጣሪዎች ነን። በልቦናችን መልካሙንም ሆነ ተቃራኒውን እንፈጥራለን። መልካም የሆንው ሁሉ፤ገና ሲፈጠር በልቦናችን ውስጥ ማበብ ይጀምራል። እንደመልካም ፅጌረዳ ይፈካል። ከልቦናችን ሲወጣ ውበቱንና መአዛውን ይዞ ይወጣል። በጎ ነገሯ ሁሉ ብርሀን ነውና  በፊታችን ላይ ይበራል።  ለተመልካቾቻችን... ለሚያየን ሁሉ በርተናል፥ ለራሳችን ደግሞ ሳንለብስ ሞቆናል። 


ለበጎ ነገር ሁሉ... ይቻላል ይቻለኛል ይሆናልም እንበል።


ቀኞቻችሁ በደስታ ይሞሉ፥ በእግዚአብሔርና በስው ዘንድ የበራችሁ ሁኑ

አሜን
Thank you so much for stopping by and 
Thank you to those of you who take the time to send me lovely e-mails with heart-warming words.

 በረከት