6.7.13

ቀስ በቀስ


ከኢትዮጵያ የመጣልኝን ሙልሙል ዳቦ ሆነ ቆሎ እስካሁን እያጣጣምኩ ነኝ። እንግዶቼም እየተስተናገዱ ናቸው። መቼም ሆነ መቼም አሜሪካን በተለይ እኔ ያለሁበት ሀገር ብዙ የሚታይና የሚኬድበት ቦታ አለ...እንግዳ ላስተናግድ ካልን ቦታዎች ሞልተውናል።

ታዲያ እንግዶቼ ይዘውት የመጡትን የቁም ቀልዶች መዝናኛና ሀገራዊ ፊልሞች ከእነሱ ጨዋታ ጋር አየሁ…ስማሁም። አዎን ኢትዮጵያችን አድጋለች። እድገቷ ደስ ሲያስኝ፥ አንዳንድ ነገሮቿ ግን ቀስ በቀስ እንቁላል የሚባለውን ተረት የዘለለች ትመስላለች። 


ኢትዮጵያችን ለዘመናት በተለይ በቴክኖሎጂና በዘመን አመጣሹ እውቀት ዳዴ ላይ የቆመች ነበረች ገና ሳትንገዳገድ ክፉውንና ደጉን ሳታውቅ ከእስራት እንደተፈታች ማፈትለኳ በጣም ያሳስባል። ደረጃ ሲወጣ አንድ ሁለቱን መዝለል ለማንም አያስደንቅም ግን አምስት አምስቱን እንጣጥ ብሎ እላይ መድረሱ ለመላላጥ ከልሆነ በስተቀር ለአድንቆት አይሆንም፥ ለእድገትም አይበጅም።
አዎን አሜሪካ ትናንት የተገኘ ነው።
አዎን እንደ ኢትዮጵያ የዘመናት ታሪክ ላይኖረው ይችላል።
 ሲያድግ ግን ቀስ በቀስ እንደልጅ ነው ያደገው።
ሲጎረምስም ቀስ በቀስ እንደወጣት ነው የጎረመስው።
አምስት አምስቱን እንጣጥ ብሎ እላይ ለመድረስ አልዘለለም፥ አንድነቱን ሕብረቱን ቴክኖሎጂውንና ዘመን አመጣሹን እውቀት እያጣጣመ አመዛዝኖ እዚህ ደርሷል፥ ባህሉን ሀይማኖቱንና ማህበራዊውን ኑሮውን በአንድ ሌሊት እርቃኑን ለማስቀረት አልሞከረም። ታድያ ኢትዮጵያችን ምን ነካት፥ ስልጣኔው ሳይገባት ልጆቿ እንጣጥ እንጣጥ ያሉት ባህላቸውንና ሀይማኖታቸውን ለመርገጥ የተቻኮሉት ለምን ይሆን? 
አረ! እንረጋጋ ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሯ ትሄዳለች እኮ


ባህልህና ሀይማኖትህ የእድገትህ ብርሀን ይሆንልሃልና አመዛዝን።

በረከት

  ­

1 comment:

  1. ታድያ ኢትዮጵያችን ምን ነካት፥ ስልጣኔው ሳይገባት ልጆቿ እንጣጥ እንጣጥ ያሉት ባህላቸውንና ሀይማኖታቸውን ለመርገጥ የተቻኮሉት ለምን ይሆን?
    አረ! እንረጋጋ ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሯ ትሄዳለች እኮ!!!!! ya.... this is also my question ???????????????????????????

    ReplyDelete