19.7.13

ማቴዎስ 11፥2 በመኪና ዘይት


ስሞኑን ብዙ ደስ የሚያስኝ ወሬዎችና ታአምራቶች እስማለሁ።አዎን አይናችንና ጆሮዎቻችንን ከከፈትን በእየለቱ በብዙ ተአምራቶች ተከበናል።እግዚአብሔር ሁልግዜ ተአምራቶችን ይስራልና።

ያጣ ሲያገኝ፥ የታመመ ሲድን፥ የደረቀ ሲለመልም በአይኔ አይቻለሁ። ከሁሉም የሚያስደንቀኝ ግን የጨለመበት ብርሀን ሲበራለት፥የጠፋው ሲመለስ ወይም ራሱን ሲያገኝ ነው። ይህንም ተአምር ለማየት ደግሞ ስሞኑን በቃሁ። የጠፋው ራሱን አግኝቶ ለምስክርነት ሲበቃ፥ ያሳለፈውን ጨለማ በእግሩ ረግጦ ደንድኖ ሲቆም፥ በሀሴት የልቡ መስኮት ስትበራ፥
 ማየት ራሱ ተስፋ እንደሆነ ተገነዘብኩ።
በዚህ አእምሮ መንቃት ላይ እንዳለሁ፥ ወደመኪናዬ ስሄድ የጎረቤቴ መኪና መቆሚያ መንገድ ላይ የመኪና ዘይት እንጥብጣቤ የስራውን ሰእል አተኩሬ ተመለከትኩት። ስእሉም ሽክም የከበደበት ስው ከነሽክሙ ተቀምጦ ያሳያልና  
እናንተ ደካሞች ሽክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ የሚለውን ቃል አስታወስኝ።
አዎን እግዚአብሔር ተአምራቶችን ከማሳየት ያቆመበት ቀን የለምና።
አይናችንና ጆሮዎቻችንን እንክፈት በማስተዋልም እንቁም። ሰለታምራቱ ሁሉ ምስጋና እናቅርብ።

ተአምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ፤ ለሕዝብህ ሀይልህን አስታወቅሃቸው።
መዝ 76፤14 Psalm 77:14


Matthew 11:28 
ማቴዎስ 11፥2Come to me, all who labor and are heavy laden, and I will give you rest.”
Matthew 11:28

ብቻውን ተአምር የሚያደርግ እግዚአብሔር በሁለንተናችሁ ሁሉ ይባርካችሁ። ሽክሞቻችሁን ሁሉ ያቅልል። እረፍቱንም ያብዛላችሁ።

አሜን
በረከት

11.7.13

ቅርጫትና ዘንቢል
cez viapsofiar

tinekhome


79ideas

sundayinbed.tumblr.com

hallway with table and mirror

makeliving

Dining Room Design

sanna&sania

Decorating with woven storage baskets and ....
INTERIOR design IMAGE CREDITS: pinterest and anordinarywoman.net 


To all of you lovely readers out there, 
To you who send me the sweetest comments and incredibly kind emails, a warm thank you and May your days are filled with spectacular blessings.  Bereket


6.7.13

ቀስ በቀስ


ከኢትዮጵያ የመጣልኝን ሙልሙል ዳቦ ሆነ ቆሎ እስካሁን እያጣጣምኩ ነኝ። እንግዶቼም እየተስተናገዱ ናቸው። መቼም ሆነ መቼም አሜሪካን በተለይ እኔ ያለሁበት ሀገር ብዙ የሚታይና የሚኬድበት ቦታ አለ...እንግዳ ላስተናግድ ካልን ቦታዎች ሞልተውናል።

ታዲያ እንግዶቼ ይዘውት የመጡትን የቁም ቀልዶች መዝናኛና ሀገራዊ ፊልሞች ከእነሱ ጨዋታ ጋር አየሁ…ስማሁም። አዎን ኢትዮጵያችን አድጋለች። እድገቷ ደስ ሲያስኝ፥ አንዳንድ ነገሮቿ ግን ቀስ በቀስ እንቁላል የሚባለውን ተረት የዘለለች ትመስላለች። 


ኢትዮጵያችን ለዘመናት በተለይ በቴክኖሎጂና በዘመን አመጣሹ እውቀት ዳዴ ላይ የቆመች ነበረች ገና ሳትንገዳገድ ክፉውንና ደጉን ሳታውቅ ከእስራት እንደተፈታች ማፈትለኳ በጣም ያሳስባል። ደረጃ ሲወጣ አንድ ሁለቱን መዝለል ለማንም አያስደንቅም ግን አምስት አምስቱን እንጣጥ ብሎ እላይ መድረሱ ለመላላጥ ከልሆነ በስተቀር ለአድንቆት አይሆንም፥ ለእድገትም አይበጅም።
አዎን አሜሪካ ትናንት የተገኘ ነው።
አዎን እንደ ኢትዮጵያ የዘመናት ታሪክ ላይኖረው ይችላል።
 ሲያድግ ግን ቀስ በቀስ እንደልጅ ነው ያደገው።
ሲጎረምስም ቀስ በቀስ እንደወጣት ነው የጎረመስው።
አምስት አምስቱን እንጣጥ ብሎ እላይ ለመድረስ አልዘለለም፥ አንድነቱን ሕብረቱን ቴክኖሎጂውንና ዘመን አመጣሹን እውቀት እያጣጣመ አመዛዝኖ እዚህ ደርሷል፥ ባህሉን ሀይማኖቱንና ማህበራዊውን ኑሮውን በአንድ ሌሊት እርቃኑን ለማስቀረት አልሞከረም። ታድያ ኢትዮጵያችን ምን ነካት፥ ስልጣኔው ሳይገባት ልጆቿ እንጣጥ እንጣጥ ያሉት ባህላቸውንና ሀይማኖታቸውን ለመርገጥ የተቻኮሉት ለምን ይሆን? 
አረ! እንረጋጋ ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሯ ትሄዳለች እኮ


ባህልህና ሀይማኖትህ የእድገትህ ብርሀን ይሆንልሃልና አመዛዝን።

በረከት

  ­