20.6.13

ሊትል ኢትዮጵያበሎሳንጀለስ የሚገኘው ሊትል ኢትዮጵያ ከመድረሳችሁ ከትንሽ ማይል በፊት፥ በጃከረንዳ ዛፍ አበባ (Jacaranda Tree)  የተሽቆጠቆጠው የፌርፋክስ የመኖርያ መንገድ፥መኪናዬን አስቁሞኝ ውበቱን አስቀረፅኝ።
Little Ethiopia, Fairfax Ave, Los Angeles, CA 90019


ስፈራችንን መንደራችንን እግዚአብሄር ይባርክልን።
በውስጡ ለምንመላለስው ለእኛ ደግሞ ከሩቅ አብቦ እንደሚታየው እንደጃከረንዳ ዛፍ በፍቅር ያበብን ያድርገን። አሜን።


በረከት
18.6.13

ተከናነባት


እውቀትን ልበሳት ጥበብን ተከናነባት

የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ይላል ቅዱስ ቃል።  
የእውቀት መጀመሪያስ? 
አንድ ሁለት ብሎ መቁጠር ነው ወይስ አቦጊዳ ማለት? 
አየርን በእጅ መጨበጥ ወይስ ጨረቃን መዳስስ?
ሚስጥራትን መፍታት ወይስ የምድርን እትብት ማግኘት።
የእውቀት መጀመሪያው ምን ይሆን?
እውቀት ኖሮኝ ጥበብ ከሌለኝ ትርፌ ምን ይሆን? ለመሆኑ የስው ብልሃቱ ጥበቡ ነው ወይስ እውቀቱ?
ተግሣፅንና ምክርን፥ጽድቅና ፍርድን፥ ትእዛዝና ህግን ጠቢብ ከጥበብ ሲያገኝ፤ በማስተዋል አንገቱ ሲደነድን፤ እውቀተኛስ ልቡ በምን ትሞላለች? መንፈሱ በምን ትጠነክራለች? መልካም እውቀት ሞገስ ብትስጥም እንኻን ሞገሷ ምን ያህል ነው?
በድሮ ግዜ አባቶቻችንን እግዚአብሔር በጥበብ የሞላቸው፤ ወንጌላቸውን ስለአወቝት ነው። የሚያዪአቸውን የሚያናግሯቸውን ወንድሞቻቸውንና እህቶቻቸውን ስለወደዱ ነው። አንዱ ስባኪ እንዳሉ
“እንደ ክርስቲያን እየለበስህ እንደ ዓለማውያን አትመላለስ” አሉ
ማለትም፤ እግዚአብሔርን እፈራለሁ አመልከዋለሁ እያልክ፤ ወንድሞችህን አትጥላ፤ እውቀትን ልበሳት ጥበብን ተከናነባት።
ማለታቸው ይሆን?

T.S. Eliot posed the question: "Where is the wisdom we have lost in knowledge? Where is the knowledge we have lost in information?"

Bereket
  
­


14.6.13

በስፋት መመልከት


 ስሞኑን ከኢትዮጵያ ትልቅ እንግዳ መጥቶብኝ ላይ ታች እያልኩ ነው። 
የሰኔ ወር ሲገባ አብሮት የሚገባው የበጋ ወቅት ነው። ታድያ ከሞቅታው አየር ጋር ማህበራዊው ኑሮ መሞቅ ይጀምራል። ስርጉ፥ ድግሱ፥ ምረቃው… ሁሉ ይቆለላል።

እኔም በዚህ ሙቀት ውስጥ ነገሮችን በጥሞና ለመመልከት ከጥግ ሆኜ ቆምኩ።


ውካታ ጫጫታ ውዝግብ ወይም መደብዘዝ በሚበዛብት ስዓት፥በፀጥታ መቆም፥ሁኔታዎችን በእርጋታ ለማጥናትና ለማየት ይረዳናል።
ላድርገው አላድርገው
ያስፈልጋል አያስፈልግም…
የመሳስሉትን ጥያቄዎች አውጥተን አውርደን መልስ እስከምናገኝ ድረስ… አዎን ነገሮችን በስፋት መመልከት አለብን።
አለበለዚያ ዓለም ያጣነውን፥ያሌለንን አጉልታ ታሳየናለች፥ከዚያ እንኻንም ዘንቦብሽ ትላለች።  ነገር ግን ከዚያ በፊት ቆም ብለን የቆምንበትን በስፋት ስንመለከት መስማት እንጀምራለን። በውካታው ውስጥ እንኻን በፀጥታ እንቆማለንና። 


Psalm 46:10 
መዝሙረ ዳዊት 45(46) ፡10