2.5.13

ቅዱስ ሳምንት:Holy Week: ዕለተ ሐሙስ


የእኛ፡የእነሱ፡የእኔ
 ሕማማት ዕለተ ሐሙስ : ጸሐፍት ፈሪሳውያን የአይሁድ ካህናት መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ጸሎተ ሐሙስ ይባላል። ትሕትናን ሊያስተምረን የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበበት፥ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱ ጠጡ በማለት ምሥጢረ ቁርባንን የመሠረተበት ቀን ነው። የጌታችን የመዳህኒታችን የእየሱስ ክርስቶስን ውለታ እያሰብን፥ በንስሓ ታጥበን፥ ለሥጋውንና ለደሙን ለመቀበል ከእርሱ ጋር በአንድነትና በኅብረት እንድንኖር ያበቃን ዘንድ፥የምንማጸንበት፤ ደጅ የምንጠናበት፤ቀን ይሁንልን።
አሜን

No comments:

Post a Comment