23.5.13

ልጄ ሆይ የአባትህን ምክር ስማ



አያቴ እንደእኛ ABCD አልቆጠረችም። የስርተፍኬት ወይም የድግሪ ምርቁም አልነበረችም ግን የጥበብን ካባ ለብሳ፥ የማስተዋልን ቆብ አጥልቃ ነበር። ለአምልኮ የሚያገለግሉት ስዕሎቿ እንደ ምስክር ወረቀት በመስታወት ተደርገው ተስቅለው ነበር።
እኔን ለማስተማር ደብተር ወይም የዘመኑን መፅሀፍት አልገለጠችም። አንደበትዋና አረማመዷ፥ ስርዓትና ህግን ይገልጥ ስለነበረ፥ራሷ የምተነበብ መፅሀፍት ነበረች። እንዲህም ሰል ፃዲቅ ላደርጋት አይደለም። እንደማንኛችንም ወድቃለች፥ እንደሁላችንም ጠባሳ ነበራት፥ ግን አንደአንዳንዶቻችን ተነስታለች።
ታድያ አያቴ የሄኔታ ምሩቅ ብቻ ብትሆንም እንኳን፥ የጥበብ እርሻ በእግሮቿ ስር፥
ተረትና ምሳሌ፥ ወግና ማዕረግ፥ ፅሎትና አምልኮ በእልፍኟ ነበሩ።
እኔም የዚህ ሁሉ ባለቤት እንድሆንላት በቁንጥጫ ብቻ ሳይሆን እንደ ሻንተዬሸ በተንጠለጠለውን አለንጋዋ ሞክራለች። ነገር ግን እርሷን በማየት የተማርኩት ይበልጣል። ቁንጥጫው ወይም ግልምጫው አያስፈልግም ነበር ሳይሆን አረማመዷን በማየት ብቻ ብዙ እንደተማርኩ ዛሬ አውቃለሁ። 

ምሳሌ 1፥1 - 6

ከወላጆቻችን ከአዃሀናቸውና ከአነጋገራቸው ብዙውን ቀስመናል። ስለዚህም ህልማቸውንና ራዕያቸውን በእኛ ያዩ ወላጆች ብዙ ናቸው። ታድያ የኛ የት ገባ? ህልሙ ቀርቶ ቅዥት በቅዥት የሆንነው ለምን ይሆን? ራዕይማ ገና በሩን (አእምሮአችን) አላንኳኳም።
ጥበበኛዋ አያቴ ከማድመጥ መስማት የምተለው አባባል ነበራት።
ማድመጥ በጆሮ፥ መስማት በልብ፥
ማድመጥ ለማወቅ፥ መስማት ለመታነፅ፥
ማድመጥ ለመታዘዝ፥ መስማት ለማድረግ፥
ማድመጥ ለዓለም፥ መስማት ለመንፈስ።
ለካስ ማድመጥና መስማት ለየቅሉ ናቸው።


እንዘርቷን ይዛ ቁጭ ብላ ስትፈትል፥ እየፈተለች ብቻ ሳይሆን እየስማችም ነበር። አዎን ከማየትም መማር ይቻላል።
 ከአፍህ እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉና ስማ፥ ስሚ።


በእግዚአብሔርና በስው ዘንድ ሞገስን አግኙ።
አሜን

በረከት

4 comments: