23.5.13

ልጄ ሆይ የአባትህን ምክር ስማአያቴ እንደእኛ ABCD አልቆጠረችም። የስርተፍኬት ወይም የድግሪ ምርቁም አልነበረችም ግን የጥበብን ካባ ለብሳ፥ የማስተዋልን ቆብ አጥልቃ ነበር። ለአምልኮ የሚያገለግሉት ስዕሎቿ እንደ ምስክር ወረቀት በመስታወት ተደርገው ተስቅለው ነበር።
እኔን ለማስተማር ደብተር ወይም የዘመኑን መፅሀፍት አልገለጠችም። አንደበትዋና አረማመዷ፥ ስርዓትና ህግን ይገልጥ ስለነበረ፥ራሷ የምተነበብ መፅሀፍት ነበረች። እንዲህም ሰል ፃዲቅ ላደርጋት አይደለም። እንደማንኛችንም ወድቃለች፥ እንደሁላችንም ጠባሳ ነበራት፥ ግን አንደአንዳንዶቻችን ተነስታለች።
ታድያ አያቴ የሄኔታ ምሩቅ ብቻ ብትሆንም እንኳን፥ የጥበብ እርሻ በእግሮቿ ስር፥
ተረትና ምሳሌ፥ ወግና ማዕረግ፥ ፅሎትና አምልኮ በእልፍኟ ነበሩ።
እኔም የዚህ ሁሉ ባለቤት እንድሆንላት በቁንጥጫ ብቻ ሳይሆን እንደ ሻንተዬሸ በተንጠለጠለውን አለንጋዋ ሞክራለች። ነገር ግን እርሷን በማየት የተማርኩት ይበልጣል። ቁንጥጫው ወይም ግልምጫው አያስፈልግም ነበር ሳይሆን አረማመዷን በማየት ብቻ ብዙ እንደተማርኩ ዛሬ አውቃለሁ። 

ምሳሌ 1፥1 - 6

ከወላጆቻችን ከአዃሀናቸውና ከአነጋገራቸው ብዙውን ቀስመናል። ስለዚህም ህልማቸውንና ራዕያቸውን በእኛ ያዩ ወላጆች ብዙ ናቸው። ታድያ የኛ የት ገባ? ህልሙ ቀርቶ ቅዥት በቅዥት የሆንነው ለምን ይሆን? ራዕይማ ገና በሩን (አእምሮአችን) አላንኳኳም።
ጥበበኛዋ አያቴ ከማድመጥ መስማት የምተለው አባባል ነበራት።
ማድመጥ በጆሮ፥ መስማት በልብ፥
ማድመጥ ለማወቅ፥ መስማት ለመታነፅ፥
ማድመጥ ለመታዘዝ፥ መስማት ለማድረግ፥
ማድመጥ ለዓለም፥ መስማት ለመንፈስ።
ለካስ ማድመጥና መስማት ለየቅሉ ናቸው።


እንዘርቷን ይዛ ቁጭ ብላ ስትፈትል፥ እየፈተለች ብቻ ሳይሆን እየስማችም ነበር። አዎን ከማየትም መማር ይቻላል።
 ከአፍህ እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉና ስማ፥ ስሚ።


በእግዚአብሔርና በስው ዘንድ ሞገስን አግኙ።
አሜን

በረከት

21.5.13

በርጩማ ጊቢ ከቤቴ


Three-legged stool: በርጩማ - Berchuma


 A thee-legged Ethiopian stool, Ethiopian artifacts. burchuma
INTERIOR design IMAGE CREDITS: pinterest

Wishing you all a really lovely week!

Bereket


17.5.13

ስም ሲያወጡ እያቆላመጡ
የዚህች አበባ ሰም በእንግሊዘኛ Lady Doorly's morning glory ይባላል። በአብዛኛውን ግዜ የዚህች አበባ ዘር (ዓይነት) አበባው፥ በጠዋት ይፈነድቅና ፀሐይ ሙሉ በሙሉ ሲወጣ አበባው ይጠቀለላል።

የእንግሊዘኛ ስሙን ወደ አማርኛ ብንተረጉመው... የወይዘሮዋ የጠዋት ቆንጅና ወይስ የወይዘሮዋ የጠዋት ክብር እንበለው?

  

በስዓሊ ቀለም ወይም በፎቶግራፍ ወረቀት ላይ ቁንጅናችን ይስነብትልናል። ዝናችንና ክብራችን ደግሞ በደራሲው ብዕር ደምቆ ይቆይ ይሆናል። ግን ፀሐይ ሙሉ በሙሉ ስትወጣ ቁንጅናችን ሲደበዝዝ፥ ክብራችንም ይቀዘቅዛል። ፀሐይ ሙሉ በሙሉ ስትወጣ... እኛም እንጠቀለላለን። ታድያ ለጠዋቱ ቁንጅናችንና ክብራችን ሰም እያወጣንለት ነው ወይስ እያስወጣንለት? ስም ሲያወጡ እያቆላመጡ እንደሚባለው ሁሉ ከመጠቅለላችን በፊት በባዶ ሜዳ የተቆላመጠ ስም ብቻ እንዳንሽከም ይስውረን።
Ipomoea horsfalliae is a flowering plant known by several common names including Lady Doorly's morning glory, cardinal creeper and Prince Kuhio vine. Most morning glory flowers unravel into full bloom in the early morning. The flowers usually start to fade a few hours before the "petals" start showing visible curling.Thank you for visiting my blog and a special thank you to all of you kind readers who take the time to leave a kind comments and e-mail, I read all your words and appreciate every one.

I hope this weekend you filled with Happiness and Flowers lining your path.
ቀኞቻችሁ በደስታ ይሞሉ፥ የማይጠወልገው አበባ በመንገዳችሁ ላይ ይነጠፍ።

 
Bereket12.5.13

Happy Mother's Day የእናቶች ቀን...

እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሳችሁ።እናት ሀገር ናት፥ እናት ማረፊያ፥መምህር፥ወዳጅ ናት... በተለይም በሃገራችን እናት አባትም እናት ሁሉንም ነች። ምክንያቱም ልጆችን የማሳደግ፥ የመንከባከብ፥ሥርዓትና ባህልን የማስያዝ ከፍተኛ ቀንበር በእናት ጫንቃ ላይ ሰለሚወድቅ እናት ብዙ ውጣ ውረድና ብዙ መከራና ስቃይ ውስጥ ታልፋለች። ምንም እንኳን በሃገራችን ­ልዩ ክብር ቢኖራትም የራሷ የሆነ የእናት ቀን የላትምና ይህ በዓል ከእለታት አንድ ቀን በሃገራችን ውስጥ በስፊው በምስጋና ቃልና በፍቅር ስጦታ የምናከብርበት ወይም የምናስብበት ቀን ይምጣልን።
Happy Mother's Day, yene fikir ,enatyie..., My Deyie, Deyieyie

And Happy Mother's day to all you mothers, grandmothers,

stepmother, daughters, sisters, aunts, and friends...

a joyful day!


Bereket


5.5.13

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን (ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሳ)
በዓቢይ ኃይለ ወሥልጣን
 (በታላቅ ኃይልና ሥልጣን
)
አሠሮ ለሰይጣን (ሰይጣንን አሰረው)
አግዓዞ ለአዳም (አዳምን ነጻ አወጣው)
ሰላም (ሰላም)
እምይእዜሰ (ከእንግዲህ ወዲህ)
ኮነ (ሆነ)
ፍስሐ ወሰላም (ደስታና ሰላም)ምስማሮቹ: መድኃኒታችን በመስቀል ላይ የተቸነከረባቸውን 
የአምስቱ የብረት ችንካሮች...ሳዶር፣ አላዶር፣ዳናት፣አዴራ፤ሮዳስ ምሳሌዎች ናቸው።

ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ።


4.5.13

ቀዳሜ ስዑር

ቀዳሜ ስዑር፡በዚህች ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሰ መቃብር ዐርፎ የዋለባት ዕለት ናትና መከራውን እናሰብ።


3.5.13

ዕለተ ዐርብ ስቀለትአምላክ ለእኛ ብሎ ቢያፈስው ደሙን
ለምን ከለከለች ፀሐይ ብርሃኗን
የከበረው ሥጋ የከበረው ደም
በመስቀል ላይ ዋለ በኢየሩሳሌም

እዩት ኢየሱስን መስቀሉ ማማሩ
ለተመራመረው ብዙ ነው ምስጢሩዕለተ ዐርብ ስቀለት፥ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልእልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን ነው፡
የበደላችንን ዋጋ የከፈለው ሊነገሩ በማይቻሉ ሕማማትን ተቀብሎ፣ተገርፎ፣ተዋርዶ፣ተሰድቦ፣ የሃጢአተኞች ምራቅ ተተፍቶበት፣ መስቀል ተሸክሞ ተራራ ወጥቶ፣ እጆቹና እግሮቹ ተቸንክረው ከመስቀል ላይ የሞትንም ጽዋ ቀምሶ ነው፡፡ አዎ! በሞቱ ሞታችንን ሻረ። በሱ ቁሰል እኛም ተፈወስን። የጌታችን የመዳህኒታችን የእየሱስ ክርስቶስን ውለታ እያሰብን፥ በንስሓ ታጥበን፥ ለሥጋውንና ለደሙን ለመቀበል ከእርሱ ጋር በአንድነትና በኅብረት እንድንኖር ያበቃን ዘንድ፥የምንማጸንበት፤ ደጅ የምንጠናበት፤ቀን ይሁንልን።
አሜን