5.4.13

አንድ አበባ ብዙ ቁንጅና


ፀደይን ለማብስር በመጋቢት ወር ብቅ ብቅ ከሚሉት አበቦች አንዱ የሁዳዴ አበባ (Lent lily) ተብሎ የሚታወቀው ዳፊደል ነው።

በክረምት ወራቶች ተኝታ የነበረችው የዚህ አገር መሬት፥በፀሐይ ለመሞቅ ራሰዋን ስታዘጋጅና ሰታነቃቃ፥አብረዋት ያሽለቡት ዘሮችና ፍሬዎች እንደገና ለመወለድ፥አዲሱን ህይወታቸውን ለመጀመር ሲጣጣሩ፥
ዳፍደል በጥሩምባው፥ፀደይ ገብቷል፥ 
የእንቅልፍ ወራት አልቛል፥ምድርም ያላትን ለመስጠት ተዘጋጅታለችና፥
ስው ሆይ ተነሳ! ስው ሆይ ንቃ!
ብሎ ያውጃል።

ታድያ! እኔም ይህንን አበባ ፎቶግራፍ ሳንሳው፥በተለያየ አቅጣጫ ውበቱን ተመለከትኩ።
ከላይ እስከታች፥ ከፊትም ከኋላም፥ ከግራም ከቀኝም፥ እንዲሁም ከውስጥ ውበቱ እጅግ ፍፁም ሆኖ አገኘሁት። ከማማሩ ሌላ ይዞ የመጣው የምስራች ዜና፥ እንዲሁም፥እንደገና የመወለድ (rebirth)፥ የአዲስ ጅመራ (new beginnings) እና የተስፋ ምልክት መሆኑ አስገረመኝ።

አንድ አበባ ብዙ ቁንጅና ብዬ... ውስጤን መረመርኩ።
ለመሆኑ እኛን ቢያገላብጡን ቁንጅናችን በየትኛው ጎናችን ነው። ውበታችን ላይ ላዩን ብቻ ያመዝን ይሆን? ከውስጣችንስ ምን አይነት ዜና ይወጣል? የአንዳችን ነፍስ ለአንዳችን ነፍስ ፀደይ ገብቷል ብላ ታበስራለችን?
ስው ሆይ ንቃ! ስው ሆይ ንቃ! ተስፋህን ያዝ። 
ስው ሆይ ተነሳ! እንደገና ጀምር ወይም እንደገና ተወለድ። 
Are you the daffodils?

1 comment:

 1. በረከት እንደምን ነሽ)  የሁዳዴ አበባ የሚፈካበት ወር ከኢትዮጵያ

  ሁዳዴ ፆም መግቢያ ጋ መገናኘቱ

  ገርሞኛል፡፡

  የሺ ነኝ

  ReplyDelete