30.4.13

ቅዱስ ሳምንት ፡Holy Week: ዕለተ ሠሉስ

የእኛ፡ የእነሱ፡የእኔ


ዕለተ ሠሉስ፡ የሕማማት ሁለተኛ ቀን፥ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ያስተማረውን ትምህርት እያስተዋልን፥ ተአምራቱንና ውለታውን እያሰብን፥
 በተለየች የመንፈሳዊ ንስሐ አምላካችን የምንማጸንበት፤ ደጅ የምንጠናበት፤ቀን ይሁንልን።
አሜን


29.4.13

ቅዱስ ሳምንት ፡Holy Week: ዕለተ ሰኑይ


የእኛ፡ የእነሱ፡የእኔ


ዕለተ ሰኑይ፡ በዚህ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን፥በበለስ ስለተመሰለው  የሰው ልጅ ሕይወትን በማሰብ፥ ሕይወታችን በከንቱ፥በቸልተኝነት እንዳይደክም እንዳይጠወልግና እንዳይደርቅ በንሰሐ የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስን ውለታ እያሰብን፥ በተለየ የመንፈሳዊ ህይወት አምላካችን የምንማጸንበት፤ ደጅ የምንጠናበት፤ቀን ይሁንልን።
አሜን

26.4.13

የዐቢይ ጾም ስምንተኛው እሑድ... ሆሳዕና

"በጌታ ስም ሆኖ መጥቶልናልና
ቡሩክ ወልደ ዳዊት ይድረስው ምስጋና
... 
በአህያ ላይ ሆኖ የስራዊት ጌታ
ገባ እየሩሳሌም በታላቅ ደሰታ
ዘንባባውን ይዘን እንዘምር በእልልታ
ሆሳዕና ለወልደ ዳዊት""አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልል በዪ፤ እነሆ፤ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያይቱ ግልገል  በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።" 
ዘካ 9፥9

"Hosanna in the highest! Blessed is He that comes in the name of the Lord!" 

Bereket


18.4.13

የማሻ ቁንጅና
ከማሻም ቁንጅና ይገኛልና
 ሁሉንም አትናቁ።

when yellow mops become yellow faces
Bereket

15.4.13

በሎሳንጀለስ መንገድ ላይ የተስቀለው ህግ


 ትናንት በሎሳንጀለስ ውስጥ በሚገኘው አንዱ ነፃ መንገድ ላይ ስነዳ፥ በስተቀኝ በኩል ያለው የቢል ቦርድ መልክት፥
ፊቴን እንደ ፀሐይ አበራው።በመጀመሪያ በላስ ቬጋስ ከዚያ ናሽፊል ቀጥሎ ጃክስንቪል አሁን ደግሞ በሎሳንጀለስ መንገድ ላይ የተስቀለው ይህ ማስታውቂያ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል”
 በሚል ርእስ ስር አስርቱን ቃላት አስቀምጧል።
ባለፉት አመታቶች ከትምህርት ቤቶችና ከማንኛውም የመንግሰት ህንፃ የተወገደው ይህ አስርቱ ቃላት ዛሬ በብዙ ሽህ የሚቆጠረው  ያመነው ሆነ ያላመነው ህዝብ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በሚለው ርዕሱ ሁሉንም እየተናገረና እያንቃቃ ነው። ማስተዋሉን ይስጠንና።
እግዚአብሔር ከከፈተ የሚዘጋ ማንም የለምና የእግዚአብሔር ህግ በአደባባይ ቆመች።ለመሆኑ አስርቱ ቃላት ምን አደረገቻችው?
ያቃናል እንጂ አያጎብጥ፥ ለምን አነሱት?

የዛሬው ትውልድ የእግዚአብሔር ህግ አይፈልጋትም፥ ኃጢያቱን ሊያደንቅ እንጂ ሊመዝን፥ እንደህጉ ሳይሆን እንደዘመኑ ለመኖር ስለሚፈልግ ፥እንኻን በልቡ ሊያኖራት በአይኑ ሊያያት አይፈልግም። ስለዚህም ከአይኑ ማራቅን ፈለገ። ታድያ የፈጣሪ ብርሀን ትጨልምበታለች። 

እኛ ህጉን  እናውቃለን የምንል ብዙዎቻችን... ተሳሰተን ወይም በድፍረት ህጉን ስበርን ፥በእግዞታ ግን ወደቅን ፥ልጅ ሳለን የእግዚአብሔር ህግ በልባችን ስሌዳ ተፅፉልና። አንዳንዶቻችን ደግሞ ህጉን ፈፅመን  ዘነጋን፥ ቸልም አልን። 
በአምላክና በእኛ መሀል፥ በእኛና በወንድሞቻችን መሀል ያለውን ይህ አስርቱን ቃላት ካላከበርን...  የምናውቃት ህግ፥ ህግ ሳትሆን ልማድ ትሆንብናለች፥ በሓላም ልማድ ሆና ትቀበራለች ፥ያኔ ጠላት ይነግሳል፥ያኔ ጠላት ይከፋል፥እግዚአብሔርም አዝኖብናልና ይተወናል።

ያን ቀን ሳይመጣ ዛሬውኑ፥ አሁኑኑ፥ ህግህ የእግሬ መብራት ለመንገዴም ብርሃን ነው ብለን ህጉን እንደገና በልቦናችን እንፃፋት፥ እናክብራትም። ለልጆቻችንም እናስተምር።


ዘጸአት 20: 1-17
Exodus 20: 1-17


Ten Commandments Painting, by Barbara Goshu

 አስርቱ ቃላት

ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ
You shall have no other gods before Me
ማቴ 4:10; 6:24; 22:37-38; ሉቃ 4:8; ራዕይ14:7.

በላይ በስማይ ካለው፥ በታችም በምድርም  ካለው፥ ከምድርም በታች በውሃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።
Thou shalt not worship Idols
ሐዋ 15:20; 17:16; 29; 1 ቆሮ 5:10-11; 6:9; 10:7, 14, 19; 12:2; 2 ቆሮ 6:16; ገላ 5:20; ኤፌ 5:5; ቘላ 3:5; 1 ተስሎንቄ 1:9; 1 ዼጥ 4:3; 1 ዮሐ 5:21; ራዕይ 2:14; 9:20; 21:8; 22:15.

የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።
Thou shalt not take the name of the Lord in vain
ማቴ 5:33-34; 1 ጢሞ 6:1; ያዕ 2:7.

የስንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።
Remember the Sabbath day, to keep it Holy
ማቴ 12:8, 12; 24:20; ማር 1:21; 2:27-28; 6:2; ሉቃ 4:16, 31; 6:5; 23:56; ሐዋ 13:14, 42, 44; 15:21; 16:13; 17:1-2; 18:4; ዕብ 4:4, 9-10

አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።
Honour your father and your mother
ማቴ 15:4; 19:19; ሉቃ 7:10; 10:19; ሉቃ 18:20; ሮሜ 1:30; ኤፌ 6:1-2; ቘላ 3:20; 2 ጢሞ 3:2.

አትግደል።
Thou shalt not Murder
ማቴ 5:21-22; 19:18; ሉቃ 7:21; 10:19; ሉቃ 18:20; ሮሜ 1:29; 13:9; ገላ 5:21;
 1 ጢሞ 1:9; ያዕ 2:11; 1ዼጥ 4:15; 1ኛ ዮሐ 3:15; ራዕይ 9:21; 21:8; 22:15.

አታመንዝር።
Thou shalt not commit Adultery
ማቴ 5:27-28; 19:18; ማር 7:21; 10:11-12, 19; ሉቃ 16:18; 18:20;  ሐዋ 21:25; ሮሜ 1:29; 2:22; 7:3; 13:9; 1 ቆሮ 5:11; 6:9, 18; 10:8; ገላ 5:19; ኤፌ 5:3;1 ተስ 4:3; ዕብ 13:4; ያዕ 2:11; 2  ዼጥ 2:14; ይሁ 1:7; ራዕይ 2:14; 2:21-22; 9:21.

አትስረቅ።
Thou shalt not Steal
ማቴ 19:18; ማር 7:22; 10:19; ሉቃ 18:20; ሮሜ 2:21; 13:9; 1ኛ ቆሮ 5:10-11; 6:10; አፌ 4:28; 1ኛ ዼጥ 4:15; ራዕይ 9:21.

በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
Thou shalt not bear false witness
ማቴ 15:19; 19:18; ማር 10:19; ሉቃ 18:20; ዮሐ 8:44; ሐዋ 5:3-4; ሮሜ 1:29; 13:9; ኤፌ 4:25; ቘላ 3:9; 
1 ጢሞ 4:2; 2  ጢሞ 3:3; ራዕይ 21:8; 22:15.

የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን  ሚስት ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንምአህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።
Thou shalt not Covet your neighbour's things
ማር 7:22; ሉቃ 12:15; ሐዋ 20:33; ሮሜ 1:29; 7:7; 13:9; 1 ቆሮ 5:10-11; 6:10; ገላ 5:19; ኤፌ 5:3, 5; 
1 ጢሞ 6:10; 2 ጢሞ 3:2; 2 ዼጥ 2:14; ዕብ 13:5.

ስለቢል ቦርድ ማስታውቂያ ጠለቅ ብለው ማወቅ ከፈለጉ...