30.3.13

“እግዜር ይማር”


ላለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ ድምፄ ተዘግቷል። ሳወራ ባለቤቴ አብሮኝ የሚያወራ ይመስላል። ሲፈጥረው ድምፄ እንደ ወራጅ ውሃ ኮለል ብሎ ወርዶ አያውቅም። ወፈርፈር ያለ ነው  እንኳንም ዘንቦብሽ… 
ከድምፅ መዘጋቱ ጋር አብሮ የተዳበለው ሳል ጉሮሮዬን ከርክሮታል።
እህቴም ሆነች ጓደኛዬ ሾርባቸውን በበርና በመስኮት አቀብለውኝ፥ “እግዜር ይማር” ብለው ሄዱ።
በበር የመጣችው ባትስተናገድም ተጫውታ ሄደች። በመስኮት ያቀበለችው… አቀበለች።
የስሩት እጆች ይባረኩ እያልኩ ሾርባቸውን አጣጥሜ ጠጣሁላቸው። ሳሉ ግን ይኽው አብሮኝ ይስላል።
በዝንጅብልና በሾርባ ያልተሽኘው ሳል... በሃገሬ መድሃኒት ልነቅለው፥ ኑጌን ቆልቼ፥ፈጭቼ አፈላሁት። ጣዕሙም እጅግ ሽጋ። 


የኑግ ዘር በእንግሊዘኛ Nyger seed ይባላል

 Nyger seed, also known as Guizotia abyssinica, crop cultivated in Ethiopia, India, Myanmar, and Nepal, and is imported into the USA primarily as bird seed for its caloric energy.

Nyger seed have good nutrient profile packed with

Protein, Fibre, Carbohydrates, Calcium, Phosphorous and Iron.
2 comments:

  1. I Hope You Get Better Soon. እግዜር ይማርሽ

    ReplyDelete
  2. በረከት ወላዲተ አምላክ ትደባብስሽ
    በጣም ደስ ይላል የሀገርሽን ኑግ አለመርሳትሽ፤

    የሺ ነኝ፤፤

    ReplyDelete