28.3.13

የፍቅር ልጆች


 Child of LOVE

በህጋቸው በልማዳቸውና በቅጣታቸው ስለጠንን። ሳቃቸውን ሳቅን፥  ቛንቛቸውን ደግሞ በከንፈሮቻችንና በልቦናችን ላይ ጠለፍነው።
ሳይገባን አረማመዳቸውን ተከተልን፥ ቀድመን ለመገኘት ሞከርን ግን ተንሽራተትን፥  በአስተሳስብ ተራርቀናልና።
አለቃቀሳቸውን አልወደድንላቸውም፥ ፍቅራቸውን ናቅን፥ አንድነታቸውንም አልተገነዘብንም፥ ህልሞቻችን ለየጋራ ነበርና።
ቁንጅናቸውን አየን እንጂ ባህሪያቸውን አልመረመርንም። አለባበሳቸውን ለበስን እንጂ ልቦናቸውን አልተጎናፀፍንም።
ላይ ላዩን ማዝገም ብቻ የኛ ስራ ሆነ።
አንገታቸው እንዴት አጠነከሩት? ራሳቸው እንዴት አላጎነበስም?
ወገቦቻቸውስ ለምን አልታጠፉም? ጉልበቶቻቸውም አልጠቆሩም? ከሁሉም በላይ ደግሞ ድምፆቻቸው እንዴት እንደዚህ ገነነ ብለን ጠይቀናል?
ላይ ላዩን ብቻ ተንጛተትን።
እጆቻቸው እንዴት ተጠማመሩ? ትከሻቸው እንዴት ተነካካ?
አይኖቻቸውስ እንዴት ተግባቡ?
ጠላቶቻቸውን እንዴት ገስፁ? የሚያስረቡሻቸው እንዴት ተቆጣጠሩ?
ይህንንስ መርምረናል?
ለመሆኑ እርካታቸው ምንድነው?
የእኛስ ጥማት?    "If you seek His help, be sure your life is clean, your motives are worthy, and you're willing to do what He asks--for He will answer your prayers."
Richard G. Scott 

No comments:

Post a Comment