19.3.13

ሙከራ አንድ ሁለትብዙ ግዜ ከማገኘው e-mail አንጻር ለሙከራ ይኸው ዛሬ በአማርኛ እጄን አነሳለሁ።

እኩለ ለሊት ካለፈ ሁለት ሰዓት ሞላ። የምድር ጉልበትና ብርታት ብቻው ተንሠራፎ የሚወስደውን ስው ይጠብቃል።
እኔም የምድርን ጉልበትና ብርታት ለብቻዬ ያለሻሞ ወስድኩ። ጸጥታውና እፎይታው ቀስ ብሎ፤ የምድርን ኅይል መመገብ የሚፈልግውን ስው ይጠብቃል።
እኔም የለሊቱን የምድር ኅይል ስውነቴ ላይ ጠመጠምኩ። የአይኔ ሽፋልፍል ሲወጠር አእምሮዬም አብሮ ተወጠረ።
በአምላኬ ቸርነት ያገኘሁትን የእጆቼን በረከቶች ተጠቀምኹ። የምድር ለሊት ኅይል አብሮኝ ቆመ።
ለመሆኑ ስንት ስው ነው የዚህ ስዓት ኅይል የሚመገበው ብዬ ራሴን ጠየቅሁ።
ለሊት ለእረፍት ተፈጥራ ሳለ ለምን ጉልበቷ እንዲህ ጠነከረ? ሙቀቷስ ለምን ይህን ያህል ሞቀ?
 ጥበብ፤ እውቀትና ፍልስፍና ለምን በለሊት ያንፅባርቃሉ?
የምድር የቀን ወይስ የለሊት ጉልበት ይበልጣል?
    I often think that the night is more alive and more richly colored than the day.”
 Vincent van Gogh quote

These blessed candles of the night”
William Shakespeare

No comments:

Post a Comment