25.3.13

አጫጭር ስነጽሁፎችA Celebration of the Short Story

ቅዳሜ ዕለት አጫጭር ስነጽሁፎችን ለማዳመጥ ወደ 400 በላይ የሚሆኑ ስዎች ገንዘባቸውን ከፍለው ተስበስቡ። በየአመቱ የሚከበረው ይህ ትሪኢት (live performances) የተጀመረው 1991 ላይ ቢሆንም ትረካው በሬድዮ ብቻ ነበር። እኔም እድለኛ ሆኜ ይኸን ለማክበር በመካከላቸው ተገኘሁ።

አራት አጫጭር የልብወለድ ፅሁፎች ተነበቡ። አንባቢያኑ ተዋናይ ነበሩና በድምፃቸው ብቻ ትረካውን አሳመሩት።

ድሮ የልጅ ጎረምሳ ሳለሁ በኢትዮዽያ ሬድዬ ይተላለፍ የነበረውን የውጋየው ደግነቱን ትረካፍቅር እስከመቃብርበአርምሞ እከታተለው ነበር። ታሪኩን ባውቀውም እንኻን በጉጉት እጠባበቀው ነበር። ታዲያ ትረካ ዛሬ ናፈቀኝ።
  
ለመሆኑ እኛ ስነጽሁፍን በስንት ገዝተናታል? እንዴትስ ጎብኝተናታል?


“A short story is a love affair, a novel is a marriage. A short story is a photograph; a novel is a film.”
Lorrie Moore

“Time is the school in which we learn, time is the fire in which we burn.”
Delmore Schwartz: American poet and short story writer

No comments:

Post a Comment